Get Mystery Box with random crypto!

የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር አብይ አህመድ ኩባንያችን በቅርቡ በዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙ | Ethio telecom

የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር አብይ አህመድ ኩባንያችን በቅርቡ በዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም ያስገነባውን የኤክስፒሪየንስ ማዕከል ጎበኙ፡፡

በጉብኝቱ ወቅት ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር የኤክስፒሪየንስ ማዕከሉ መገንባት በጣም አስፈላጊ እና በጥሩ ሁኔታ የተገነባ መሆኑን በመግለጽ ማዕከሉ የወጣቶችን የፈጠራ ክህሎት የሚያነሳሳ፣ በዲጂታል ሥነ-ምህዳሩ የተሰማሩ ተዋናዮች አዳዲስ የዲጂታል ቴክኖሎጂዎችን በተግባር የሚሞክሩበት እና ወደ ፈጠራ የሚቀይሩበት ማዕከል መሆኑን ገልጸዋል፡፡

አክለውም የኤክስፒሪየንስ ማዕከሉ ለሀገራችን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን መፋጠን እና ሁለንተናዊ እድገት አስቻይ ሁኔታዎችን ለመፍጠር ከፍተኛ ሚና የሚኖረው መሆኑን በመረዳት፣ ወጣት የቴክኖሎጂ አልሚዎች ያላቸውን ራዕይ ለማሳካት በር የሚከፍትላቸው መሆኑን እንዲሁም የተለያዩ ተቋማት ማዕከሉን በመጎብኘት የተግባር ተሞክሮዎችን ማከናወን የሚችሉበት መሆኑን በመግለጽ ማዕከሉን ሊጎበኙት እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ በአድዋ ሙዚየም የገነባነውን ኤክስፒሪየንስ ማዕከላችን በመጎብኘት ስለሰጡን ግብዓት እና አበረታች አስተያየት ከልብ እናመሠግናለን፡፡

#DigitalAfrica #DigitalEthiopia #SmartAfrica @PMEthiopia #GSMA #ITU