Get Mystery Box with random crypto!

ይህ በተለምዶ ፕላምፕሌት (plampy nut) የሚባለው የታሸገ ምግብ ልጣች በዩንቨስቲያችን ዶርም | Ethio techs Link

ይህ በተለምዶ ፕላምፕሌት (plampy nut) የሚባለው የታሸገ ምግብ ልጣች በዩንቨስቲያችን ዶርም ወለል ላይ መመልከት የተለመደ ከሆነ ሰነባብቷል። ቴሌግራም ግሩፖች እና ቻናሎች ላይ ለጉድ ማስተዋቂያ ይሰራባቸዋል ፤ ከ23 እስከ 40 ብርም ይሸጣሉ... በሽንፋኑ ላይ መመልከት እንደሚቻለው ለምግብ እጥረት ለገጠማቸው ህፃናት በአሜሪካኑ የእርዳታ ድርጅት USAID የተዘጋጀ ነብስ አድን ምግብ ነው።

የአሜሪካን መንግስት ከሁለት ሳምንት በፊት ወደኢትዮጵያ በተለይም ወደ ትግራይ የሚልካቸው የእርዳታ ምግቦች ለተገቢው አላማ እየዋሉ ስላልሆነ እርዳታውን እንዳቆመ ተናግሮ ነበር። ቃል በቃል "በዚህ ሁኔታ መቀጠል ስለማይቻል፣ አስቸጋሪ ነገር ግን አስፈላጊ ውሳኔ አሳልፈናል” የሚል መግለጫ ነበር የሰጡት።

ይህ በእንዲህ እንዳለ አሁንም ከትግራይ በየቀኑ በርሀብ የሚሞቱ ትዎች እናዳሉ ሪፖርቶች ይወጣሉ። ለተራበ ሰው የመጣን ምግብ ከረሀብተኛ ጎሮሮ ላይ ነጥቆ ከመሸጥ በላይ ምን አይነት ጭካኔ ሊኖር እንደሚችል አላውቅም። ጉዳዩ ከታች ባሉ ሰዎች የሚፈፀም ድርጊት ስለሆነ እነሱ ላይ የእርምት እርምጃ ይወሰድ እንዳንልም።

በረሀብ ለተጎዱ አከባቢዎች የመጣው እህል ከነ ለጋሽ ሀገራቱ ባንዲራ ያረፈበት ከረጢት በመንግሰት ደረጃ ወደውጭ ሀገራት ሲላክ ተመልክተናል። Export አረግን እያልን የምንፎክርበት ስንዴ ባይደርሳቸው እንዴት በእርዳታ ያገኙትን ከልክለን በረሀብ እንዲሞቱ እንፈርድባቸዋለን?

                   #Share
@ethio_techs @ethio_techs