Get Mystery Box with random crypto!

የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት መቼ ይገለፃል ? በርካታ ተማሪዎች እና የተማሪ ወላጆች በሁለት | ኢትዮ Students News

የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት መቼ ይገለፃል ?

በርካታ ተማሪዎች እና የተማሪ ወላጆች በሁለት ዙር ለመጀመሪያ ጊዜ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተሰጠው የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ይፋ የሚደረግበትን ቀን እየጠየቁ ይገኛሉ።

የፈተናው ውጤት መዘግየቱን የሚገልፁት ተማሪዎች እና ወላጆች ትምህርት ሚኒስቴር ውጤቱ መቼ ይፋ እንደሚደረግ እንዲያሳውቅ ጠይቀዋል።

" የትምህርት ዓመቱ እየገፋ ነው ፤ ገና ከውጤት በኃላ ምደባ አለ ፤ ልጆቻችን ከመደበኛ ትምህርት ርቀው ቤት ከሆኑ በርካታ ሳምንታት አልፈዋል ፤ የሁሉም ውጤት ከ2ኛ ዙር ተፈታኞች ጋር ይገለፃል ቢባልም ዛሬም ድረስ ቀኑ መቼ እንደሆነ አይታወቅም ፤ የተማሪዎችን የትምህርት ዓመት ታሳቢ በማድረግ ቀኑ ቢገለፅ " ሲሉ ወላጆች መልዕክታቸውን ልከዋል።

መልዕክት የላኩልን አንድ የትምህርት ሚኒስቴር አመራር ፤ ምንም እንኳን ቁርጥ ያለው የውጤት መግለጫ ቀን ባይታወቅም ነገር ግን ከጥር 15 ጀምሮ ባሉት ቀናት ሊሆን እንደሚችል ጠቁመዋል።

ለመጀመሪያ ጊዜ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ የተሰጠውን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከ930 ሺ በላይ ተማሪዎች መውሰዳቸው መገለፁ የሚዘነጋ አይደለም።
@leyumerga