Get Mystery Box with random crypto!

'የተከፈተብንን ጦርነት በጀግንነት እየመከትን የግብርና ሥራችን ተጠናክሮ ይቀጥላል!' - አማራ ክል | ኢትዮ Students News

"የተከፈተብንን ጦርነት በጀግንነት እየመከትን የግብርና ሥራችን ተጠናክሮ ይቀጥላል!" - አማራ ክልል

አሸባሪው ህወሓት ይህን ወቅት ለጦርነት የሚመርጠው የሀገሪቱ የኢኮኖሚ የጀርባ አጥንት የሆነው የግብርና ዘርፉን ሆን ብሎ ለማዳከም ጭምር መሆኑን የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ ገለጸ።

አርሶ አደሩን ከግብርና ሥራው አስተጓጉሎ ሕዝብን ለማስራብ እና ኅልውናውን ለማጥፋት፤ ኢትዮጵያን ደግሞ እንደ ሀገር በኢኮኖሚ ደካማ አድርጎ ራሷን መከላከል እንዳትችል በማድረግ ሀገሪቱን ለማፍረስ አስቦ የፈፀመው ጥቃት ነው ብሏል።

አክሎም፣ ይህን የጥፋት ተልዕኮ ለመመከት ጥምር ጦሩ በጀግንነት እየመከተ ይገኛል መላው ሕዝቡም ደጀንነቱን እያሳየ መሆኑን ገልጿል።

"ሌላኛው የህልውና የፍልሚያ ግንባር የግብርና ልማት በመኾኑ፤ በዚሁ ግንባር የተሰለፋችሁ አመራሮች፣ ባለሙያዎችና መላው አርሶ አደሮች በእልህና በቁጭት ያለንን አቅም ሁሉ ተጠቅመን በሰብል ጥበቃ በተለይ አረም ማረምና ተባይ አሰሳ ማድረግ፤ የተተከሉ ችግኞች መንከባከብ፤ በቀሪ እርጥበት ለሚዘሩ ሰብሎች ትኩረት መስጠት፤ የተፈጥሮ ማዳበሪያ ኮምፖስት ዝግጅት አጠናክሮ መቀጠል፤ ለቀጣይ ዓመት መስኖ ልማት ቅድመ ዝግጅት ማድረግና ሌሎች ስራዎች ላይም ከፍተኛ ርብርብ ማድረግ አለብን" ሲል ቢሮው አሳስቧል።

ምንጊዜም ቢሆን ፈተና ውስጥ ብንሆን፤  ችግር ቢያጋጥመን፤ ጦርነት ቢታወጅብን በጀግንነት እየተፋለምን ፤በፅናት እየመከትን ከግብርና ሥራችን ለአፍታም ቢሆን አይናችንን አንነቅልም ሲል ቢሮው በማህበራዊ ትስስር ገጹ አስታውቋል።