Get Mystery Box with random crypto!

የ9ኛ እና 10ኛ ክፍል አዲሱ ሥርዓተ ትምህርት በበ2015 ዓመት ቀጣይ አመት ለሙከራ ይሰጣል!! | ኢትዮ Students News

የ9ኛ እና 10ኛ ክፍል አዲሱ ሥርዓተ ትምህርት በበ2015 ዓመት ቀጣይ አመት ለሙከራ ይሰጣል!!

የ9ኛ እና 10ኛ ክፍል አዲሱ ሥርዓተ ትምህርት የሙከራ ትግበራ በተመረጡ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ላይ በ2015 ዓመት እንደሚጀመር የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ አስታውቋል።አዲሱ የስርዓተ ትምህርት ዝግጅት በርካታ ደረጃዎችን አልፎ ለሙከራ ትግበራ የደረሰ መሆኑን የስርዓተ ትምህርት ማበልፀጊያ መሪ ስራ አስፈፃሚ ዶክተር ቴዎድሮስ ሸዋርገጥ ለብስራት ሬድዮ ገልፀዋል ።

በስርዓተ ትምህርት ዝግጅቱ ላይ የተመረጡ የመማር ማስተማር የልህቀት ማዕከላት ዩኒቨርሲቲዎች እና ካምብሪጅ ዩኒቨርስቲ በአማካሪነት እንደተሳተፉበት ሥራ አስፈፃሚው ገልፀዋል ።ይህ ሥርዓተ ትምህርት ሀገር በቀል እውቀትን፣ ግብረ ገብነትን ፣ ሳይንስና ቴክኖሎጂን የተላበሰ እንዲሆን ተደርጎ የተዘጋጀ መሆኑን ገልፀዋል ።

በመሆኑም በዚህ የሙከራ ትግበራ ወቅት ከመምህራንና ከባለድርሻ አካላት በርካታ ግብዓቶች እንደሚሰበሰቡ ጠቅሰው ወላጆችና ሌሎችም አስተያየት እዲሰጡበት በድረ ገፅ ይለቀቃል ተብላል።በሙከራ ትግበራው ወቅት የሚመጡ አስተያየቶች ተካተው በ2016 ወደ ሙሉ ትግበራ እንደሚገባም ተገልጿል ።