Get Mystery Box with random crypto!

በአዲሱ ረቂቅ የትምህርት ፖሊሲ ከቅድመ አንደኛ እስከ ስምንተኛ ክፍል ትምህርት ነፃ እና አስገዳጅ | ኢትዮ Students News

በአዲሱ ረቂቅ የትምህርት ፖሊሲ ከቅድመ አንደኛ እስከ ስምንተኛ ክፍል ትምህርት ነፃ እና አስገዳጅ ይሆናል፡- የትምህርት ሚኒስቴር
****

በአዲሱ ረቂቅ የትምህርት እና ጥናት ፖሊሲ ከቅድመ አንደኛ እስከ ስምንተኛ ከፍል የሚሰጥ ትምህርት ነፃ እና አስገዳጅ እንደሚሆን የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ።

በአዲሱ የትምህርት ፍኖታ ካርታ ግኝት መሰረት ዜጎች ከቅድመ አንደኛ እስከ ስምንተኛ ክፍል በግዴታ እንዲማሩ ለማስቻልና የትምህርት አሰጣጥ ሂደቱን የተሳለጠ ለማድረግ አጠቃላይ የትምህርት ረቂቅ አዋጅ ተግባራዊ እንደሚደረግ በሚኒስቴሩ የስርዓተ ትምህርት ማበልፀጊያ ክፍል ኃላፊ ዶ/ር ቴዎድሮስ ሸዋረገድ በተለይ ለኢቢሲ ሳይበር ሚዲያ ገልጸዋል።

ፍኖተ ካርታውን ለማዘጋጀት ሲሞከር የትምህርት ዘርፉ ያለበትን ሁኔታ ሊያሳይ የሚያስችል ጥናት መደረጉን የተናገሩት ኃላፊው፤ መንግስት ለትምህርት ፍትሃዊ ተጠቃሚነት እና ጥራት ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት በአዲስ መልክ ፍኖተ ካርታ አዘጋጅቶ ወደ ትግበራ መግባቱን ገልፀዋል።