Get Mystery Box with random crypto!

ትምህርት ሚኒስቴር የፈተና ስርቆትን ለመከላከል ፈተና በኦንላይን ታብሌቶችን በመጠቀም ዝግጅት ላይ | ኢትዮ Students News

ትምህርት ሚኒስቴር የፈተና ስርቆትን ለመከላከል ፈተና በኦንላይን ታብሌቶችን በመጠቀም ዝግጅት ላይ ነው

የትምህርት ሚኒስትር ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ዛሬ ለህ/ተ/ም/ቤት ከሰጡት ማብራሪያ የተወሰደ

ባለፈው ዓመት ተጀምሮ የነበረውን የ12ኛ ክፍል ፈተናን በታብሌት ለመስጠት የተጀመረውን ስራ በከፍተኛ ደረጃ እየገፋንበት ነው ።

ወደ 1 ሚሊዮን ታብሌት ሃገር ውስጥ ለማስገባት ወደ 460 ሚሊዮን ዶላር ይጠይቃል፤ ይሄን ከቻይና መንግስት ጋር በሚደረግ ንግግር በእርዳታ ሊመጣ የሚችልበትን መንገድ በብዙ መንገድ ጠ/ሚኒስትሩም ገብተውበት እየገፋን ነው " ብለዋል።

" እሱ እንኳን ቢያቅተን በዚህ ዓመት የምንችለውን ሁሉ ሞክረን የምንወስደው እርምጃ ግን አንዱ በየትምህርት ቤቶቹ ፈተናን መፈት ትተን የሚያስወጣንን ወጪ አውጥተን ተማሪዎቹን ከየትምህርት ቤታቸው አምጥተን በየዩኒቨርሲቲ ማዕከላት ውስጥ ፈተናዎቹን እንዲወስዱ ማድረግ ነው ፤ ይሄን ነው አንዱ ልንሄድበት እያሰብን ያለነው " ብለዋል።

አክለውም ፤ በቀጣይ አመት የሚጀመረው የመውጫ ፈተና የተገባበት አንድ ተማሪ ከታችን ያለውን አጭበርብሮ አልፎ ቢመጣ ኮሌጅም ከገባ በኃላ እንደገና ፈተና እንደሚጠብቀው አውቆ ቢያንስ ኮሌጅ ከገባ በኃላ በደንብ ተምሮ እንዲያውቅ ነው ብለዋል።

#ሼር

• ይቀላቀሉን •
https://t.me/+2g72gKcjS_E4Mjdk
https://t.me/+2g72gKcjS_E4Mjdk