Get Mystery Box with random crypto!

ሩዲገር PREE - MATCH PRESS CONFRERES ! በቼልሲ ሆነህ ከሪያል ማድሪድ ጋር | ኢትዮ ሪያል ማድሪድ

ሩዲገር PREE - MATCH PRESS CONFRERES !

በቼልሲ ሆነህ ከሪያል ማድሪድ ጋር በበርናባው ስላደረከዉ የቻምፒየንስ ሊግ ጨዋታ ?

"ባለፈው የውድድር አመት ከሪያል ማድሪድ ጋር ያደረኩት የመልስ ጨዋታ በጣም ከባድ ነበር። ባለፈው የውድድር አመቴ የሪያል ማድሪድ ተቀናቃኝ ሆኜ በበርናባው ተጫውቻለዉ አሁን ግን የሪያል ማድሪድ ተጨዋች ሆኛለው በነገው ጨዋታ ለቡድኑ ስኬት ሁሉንም ነገር እሰጣለዉ። እንደ ሪያል ማድሪድ ተጨዋች በበርናባው በመገኘቴ በጣም ደስተኛ ነኝ።"

"በበርናባው ከሪያል ጋር ስትጫወት ከሌሎቹ ጨዋታዎች በተለየ ሁኔታ ላይ ሆነዉ ይገጥሙሀል። አሁን የሪያል ማድሪድ ተጨዋች በመሆኔ ኩራት ይሰማኛል እናም ከቤንዜማ ፣ ሞድሪች እና ከሌሎች ከዋክብቶች ጋር በመጫወቴ ፍፁም ደስተኛ ነኝ። እውነት ለመናገር በሪያል ማድሪድ መጫወት ከየትኛውም ቡድን የተለየ ነው። በሪያል ማድሪድ ኩሩ ታሪክ ምክንያት በሁሉም ውድድር ማሸነፍ እና ሻምፒዮን መሆን አለብህ። እዚህ ያለው ጫና በጣም ከፍተኛ ነው እናም በእርግጥ ከመጀመሪያው ቀን ጀምሮ ይህንን አውቄ ነበር። ነገር ግን ሁኔታውን ስትለምደዉ ሁሉም ነገር ቀላል ይሆናል።"

ስለ ቪኒስየስ ዡኒየር ፦

"ቪኒ በጨዋታው ላይ ማተኮር አለበት ፣  አሁንም በጣም ወጣት እና ችሎታ ያለዉ ተጨዋች ነው። እናም ከአመት አመት የተሻለ ይሆናል። በተረፈ አጠገቡ ካሉት ኮከቦች ብዙ ይማራል።"

ስለነገው የሊቨርፑል ጨዋታ ፦

"የመጀመሪያዎቹን 15 ደቂቃዎች ችላ ብለን የአንፊልድ አጋጣሚ እንዲደገም አናደርግም። በዚህ የጨዋታ ደረጃ ላይ ጎል ማስቆጠር በጣም አስፈላጊ ነው። ለሊቨርፑል ሙሉ ክብር ይዘን ወደ ሜዳ መግባት አለብን። በመጀመሪያዉ ዙር ጨዋታ በአንፊልድ ጥሩ አጀማመር አልነበረንም ፣ እና ሁኔታዎች በበርናባው የተለየ መሆን አለባቸው። በማጥቃት እና በመከላከል ላይ ሚዛኑን መጠበቅ እና በመጀመሪያው አጋማሽ ጠንክሮ መጫወት በጣም አስፈላጊ ነው።"

@ETHIO_REAL_MADRID_14
@ETHIO_REAL_MADRID_14

ግሩፓችንን ይቀላቀሉ

https://t.me/+Uogf2-3bOBjpolkk