Get Mystery Box with random crypto!

#ኸሚስ_አመሻሹ_ላይ! ነብዬ ወደ መዲና ዘልቀው መስጂዳቸውን ገነቡ። ሶሀቦቻቸውን አስተባብረው አስ | Ethio Neshida & Menzuma

#ኸሚስ_አመሻሹ_ላይ!

ነብዬ ወደ መዲና ዘልቀው መስጂዳቸውን ገነቡ። ሶሀቦቻቸውን አስተባብረው አስዋቡት። ከቴምር ግንድ እና ግንብ አዋቀሩት። ከዚያም ከሚህራባቸው አጠገብ የቴምር ግንድ ተተከለላቸው። በጁምዓ እለት እየተደገፉት ኹጥባ ያደርጋሉ፣ ትምህርት ይሰጡበታል፣ ጊዜ ያሳልፉበታል፣ ለዚክር ይመርጡታል፣ ውሏቸውን ከእርሱ ጋር አስተሳስረዋል። ታዲያ በጁምዓ እለት ለኹጥባም ሆነ በአዘቦት ለትምህርት እዚያ ቆመው መድደገፋቸው እንዳያደክማቸው የሰጉት ሶሀቦች ባለሶስት ደረጃ መቀመጫ ያለው ከፍ ያለ ሚንበር ገነቡላቸው። በዚያም ጊዜ ወዳጄዋ ነቢ ወደ ሚንበሩ ዘልቀው ለኹጥባቸው ተሰናዱ።

ያ የቴምር ግንድ ታድያ የሚወደው ድምፃቸው ቢሸሸው፣ የሚጥመው ወዛቸው ቢርቀው ተከዘ። የሚያምረው ሽታቸው ቢለዬው ሀዘን አቆራመደው። እጅጉን ሳሳ። ሁለት ወይም ሶስት ክንድ ብቻ ፈቀቅ ያሉበትን ነብይ ናፈቀ። ሙሉ መስጂዱን ያዳረሰ የለቅሶ ድምፁን ከታፈነበት ለቀቀው። አሏህ ምላስ አዋሰው። ድምፅ አወጣ። ሶሀባዎች ግራ ተጋቡ። ነብዬዋ ቢያዩት ጊዜ እያለቀሰ ነው። ወዲያውኑ ልጇ ያለቀሰባት እናት ሳስታ እንደምትሄደው ወደዚያ የቴምር ግንድ ሄዱ። እቅፍ፣ ድግፍ አደረጉት። አባበሉት። ሳሙት። እያሻሹ "አይዞህ" አሉት። እንደ ህፃን ልጅ ተረጋጋ። የሚገርም ነገር ነው። የቴምር ግንድ እንዲህ ለአፍታ ብሎም ለጥቂት ክንድ ርቀት ሸሸት ቢሉት ጊዜ ፈራ። ቀጠሉ ሰይዲ ነብዬዋ። "በዱንያ ላይ እያፈራ ሰዎች ከእርሱ የሚመገቡት የቴምር ዛፍ ትሆናለህ ወይስ በአኼራ ከእኔ መጎራበትን ትመርጣለህ?" ብለው ውድ ሀሳብ አቀረቡለት። እንዴት ያሉ ነብይ ናቸው? እንዲህ ለሚሳሳ የቴምር ትኩረት ሰጥተው ያባበሉት ምንኛ ቢያምሩ ነው?
በላጩን ያወቀ አፍቃሪ ነበርና "በጀነት ከአንቱ ልጎራበት" ብሎ መረጠ። ታደለ። አሏህ አላቀው። ሰይዲ ሀሰኑል በስሪይ ይህንን ሀዲስ በቀሩ እና ባስታወሱ ጊዜ እያለቀሱ "ያ የቴምር ግንድ እጅጉን ናፍቀውት ካለቀሰ፣ እኛ ከእርሱ ይበልጥ ልናለቅስ የተገባን አልነበርንምን?" ይላሉ። ንግግራቸው እውነት ነው። እኛ ልናለቅስ ይገባ ነበር።

ኒያውን ያሳመረ የቴምር ግንድ በጀነት ታችኛው ሳይሆን ከአዕላው ተሹሟል። ፍቅር ሲያሞናድል፣ ናፍቆት ሲያደላድል እንዲህ ያሳምራል። ነብዬዋ ብናለቅስባቸው የማይተውን ናቸው። እንኳን ለዱንያው ለአኼራው ጭንቀታችን አደራረሳቸው ከመብረቅ ይፈጥናል። ስማቸው ለተራበ ቀለቡ፣ ለተጠማ ዘምዘሙ፣ ለበረደው ሙቀቱ፣ ለተረበሸ ሰላሙ ነው። በቁጥቦቹ ተገንብቶ በኑር ላይ በቆመው ኑር መስጅድ ውስጥ ያሉት ኑራማዎች በሙሉ የነቢን አሰር የምናይባቸው፣ መዲናን የምናስታውስባቸው ናቸው። ለ‘ኛ ከነሱም ሆነ በተቂዮች ከተሞላው መስጅድ መንነጠል ህመሙ እንደ ቴምሩ ግንድ ነው። ለ‘ኛ የአቡል ጀበል ፍልቃቂው ኑር መስጅድ ማለት ሰይዳችን "እኛም እንወደዋለን፤ እሱም ይወደናል" እንዳሉት ጀበል ነው።

#ሶሉ_ዓለል_ሐቢብ!
አሏሁመሶሊ ወሰሊም ወባሪክ ዓላ ሰይዲና ወመውላና ሙሐመድ ወዓላ አሊሂ ወሶህቢሂ ወሰለም!
Atiqa Ahmed Ali