Get Mystery Box with random crypto!

ከዋኪብ ከዋኪብ በሚል መጠሪያ በመልካም ወንድማዊ ትስስር በአይነቱ ልዩ የሆነ የጥበብ መ | Ethio Neshida & Menzuma

ከዋኪብ
ከዋኪብ በሚል መጠሪያ በመልካም ወንድማዊ ትስስር በአይነቱ ልዩ የሆነ
የጥበብ መድረክ ይዘንላቹ ወደ እናንተ ለመምጣት መሰናዶ ከጀመርን ወራት ተቆጥረዋል
ዐላማችንን አዉቀን :ራዕይ ለይተን
ግባችን መዳረሻችን እሩቅ መሆኑን ተገንዝበን
ከአላህ ሱብሀነ ወተዐላ በተሰጠን
የኪነ ጥበብ ተሰጥኦ ዘርፍ ዑማዉን ለማገልገል የድርሻችንን አሻራ ለማሳረፍ ዲኑን ለመኻደም እንሆ በጀመዐ ሆነን ለመስራት በአላህ ፈቃድ በመልካም እሳቤ እና በጥሩ ኒያ ተጣምረን ለመስራት በአብሮነት ተነስተናል
በዚህ ከዋኪብ አባላት ማእቀፍ ዉስጥ ሶስቱ ማዲሆች
ሰልሀዲን ሁሴን
አሚር ሁሴን
ፉአድ ሸምሱ
እንዲሁም ሁለቱ ገጣሚያን
ዑስታዝ ሰኢድ አህመድ እና
አብዱልመሊክ ላሊ (ጎራዉ)
በአንድነት ተጣምረዋል
ይህ ልዩ የጥበብ መድረክ ፕሮግራም በአላህ ፈቃድ በቅርብ ግዜያት ወደ እናንተ ይደርሳል ።