Get Mystery Box with random crypto!

የእርዳታ ጥሪ አሰላም አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱ በመላው አለም የምትገኙ እህት ወንድሞቼ የ | Ethio🇪🇹Muslim🇪🇹 Nashida - Menzuma 🎼

የእርዳታ ጥሪ

አሰላም አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱ በመላው አለም የምትገኙ እህት ወንድሞቼ የአላህ ሰላም በናንተ ላይ እንዲሆን እየተመኘው ዛሬ የሁላቹንም ትብብር እሻለው!

አንድ ጎረቤታችን ከአመታት በፊት ነበር ከሚቱና ልጆቹ ጋር እኛ ሰፈር ቤት ገዝቶ የገባው ከዛም አነስ ያለች ሱቅ ከፍቶ ከሱ በሚገኘው ገቢ ቤተሰቦቹን ያስተዳድርበታል ዘንድሮ 2015 ጅማሮ ላይ ሚስቱ በጠና ታማ ከወር በላይ ሆስፒታል ተኛች በጣም ብዙ ብር አውጥቶ አሳከማት አልተሻላትም ነበር በመጨረሻም ሲህር ተብላ ቁርዓን አስቀርቶባት ተሻላት ትንሽ እንደቆየም የ5 አመት የሚሆን ልጁን በጠና ተመመበት አሁንም በጣም ተቸገረ ወላሂ አል አዚም ብር አጥቶ የኔ ቤተሰቦችና የሰፈራችን ሰዎች ትንሽ ብር አዋተው ልጁም ታክሞ በአለህ ፍቃድ ተሻለው። ነገር ግን አህባቢ ወላሂ ያኔ እንደዛ ሙሉ እቃ ያለው ሱቅ አሁን እጅግ በጣም ትንሽ እቃዎች ነው ያሉት ካርድ እራሱ የለም ወላሂ ረመዳንን እራሱ በጣም ተቸግረው ነው እያሳለፉ ያሉት።

እና ውዶቼ ይነኝህን ሚስኪን ቤተሰቦች ችግር ሁላችንም ብንተባበር  መቅረፍ እንችላለን በአላህ ፍቃድ ወላሂ።

እስከ ረመዳን 29 ድረስ የሚቆይ  ለዚህ ቤተሰብ ኢዳቸውን ደስ ብሏቸው እንዲያሳልፉ የገቢ ማሰባሰቢያ ከስር በሚታዩት አካውንት የቅማችሁን እንድታግዙን በአላህ ስም እንጠይቃለን።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

1000512156669

Dawud Muhammad Shalo