Get Mystery Box with random crypto!

ታፋጭ የትዳር ታሪክ ከእለታት አንድ ቀን አንዲት ወጣት በትዳሯ ተስፋ ትቆርጣለች ። ባሏንም ለመግደ | Ethio🇪🇹Muslim🇪🇹 Nashida - Menzuma 🎼

ታፋጭ የትዳር ታሪክ
ከእለታት አንድ ቀን አንዲት ወጣት በትዳሯ ተስፋ ትቆርጣለች ። ባሏንም
ለመግደል ታስባለች። ማታውን ስታሰላስል ታድርና ጧት ላይ እንዴት ማንም
ሰው በማይጠራጠረውና እርሷንም ወንጀለኛ በማያስደርጋት መልኩ መግደል
እንደምትችል ለመመካከር እናቷ ጋር ትሄዳለች።እናቷም "ማንም
በማይጠረጥረው መንገድ እንድትገይው እረዳሻለሁ። ግን አንቺም ማድረግ
ያለብሽ ነገሮች አሉ።
1ኛ መጀመሪያ ከባልሽ ጋር መታረቅ አለብሽ። ምክንያቱም ከሞተ በኋላ በፊት
ፀብ ካልነበረሽ ማንም አይጠረጥርሽም
2ኛ ራሰሽን መጠበቅና ለባልሽ ቆንጆ ሆነሽ መታየት አለብሽ
3ኛ ጥሩ እንክብካቤና አድናቆት ስጪው። ያሰብሽውን እንዳይጠረጥር
ያደርገዋል።
4ኛ ትዕግስተኛ ሁኚ።ፍቅር ሰጪው። ቅናት ቀንሺ።የሚናገረውን ጆሮ ሰጥተሽ
አዳምጪው።
እነዚህን ነገሮች ማድረግ ትችያለሽ?"ብላ ጠየቀቻት እናቲቱ።
"ምንም ችግር የለውም። እማ ብቻ እርሱን የምገድልበትን መንገድ ንገሪኝ።"
አለች ልጅቷ።
"እንደዚያ ከሆነ ምን ማድረግ እንዳለብሽ እነግርሻለሁ። በደንብ
አድምጪኝ።"አለች እናት።ልጅቷም በአትኩሮት መስማት ጀመረች።
"ይህንን መርዝ በምግቡ ውስጥ በየቀኑ ትንሽ ትንሽ ጨምሪ ቀስ በቀስ
እያዳከመው ይገድለዋል።" አለቻት። ልጅቷም መርዙን ይዛ በደስታ ቤቷ ሄደች።
በተነገራት መሰረትም ለባሏ መስጠት ጀመረች።
ከወር በኋላ እንደገና እያለቀሰች እናቷ ጋር መጣች። "እማ አሁን ባለቤቴን
መግደል አልፈልግም።በጣም ተለውጧል። እንደያውም ለርሱ ያለኝ ፍቅር ከቀን
ቀን እየጨመረ ነው።እባክሽ እማ መርዙ እንዳይገድለው ምን ላድርግ?ያለ እርሱ
መኖር አልችልም። አለች ስቅስቅ ብላ እያለቀሰች።
እናትም "አይዞሽ ልጄ አታልቅሺ የሰጠሁሽ መርዝ አልነበረም።የደቀቀ ስኳር ነበር።
በርግጥ መርዝ የነበርሽው አንቺ ነበርሽ። ያ ነበር ባለቤትሽን ቀስ በቀስ
እየገደለው የነበረው። አየሽ አይደል ፍቅርና እንክብካቤ ስትሰጪው እንዴት
አይነት መልካም ሰው እንደሆነ።ስለዚህ ከዚህ ተምረሽ ለባልሽ መልካም ሚስት
ሁኚለት።"ብላ ነገረቻት።
የኔ እህት ወንድ ልጅ የፈለገ አረመኔ ቢመስል ልቡ ገራገር ነው በፍቅር
ልታሸንፊው ትችያለሽ። መልካም ሚስት ሁኚለት ያሉትን አስታወሰኝና በረኪናውን
ወደፍቅር የምትቀይርበትን መንገድ ፈልግ ምክሬ ነው።
@Ethio_Muslim_Nashida