Get Mystery Box with random crypto!

አስቸኳይ መልዕክት ነው። ሼር አድርጉት በጎንደሩ ጥቃት ሌሎች አከባቢዎች ያሉ ክርስትያን ወንድሞቻ | Ethio🇪🇹Muslim🇪🇹 Nashida - Menzuma 🎼

አስቸኳይ መልዕክት ነው። ሼር አድርጉት

በጎንደሩ ጥቃት ሌሎች አከባቢዎች ያሉ ክርስትያን ወንድሞቻችን ተጠያቂ አይደሉም፣ ልንጠብቃቸው ይገባል!

ጎንደር ለተፈጸመው ድርጊት ተጠያቂው ጥቂት የጎንደር አክራሪ እንጂ በሌሎች አከባቢ ያሉ ክርስትያን ወንድም እህቶቻችን አይደሉም።

ስለዚህም በየትኛውም ቦታ የሚገኙ የክርስትና እምነት ተከታይ ወንድም እህቶቻችን፣ ወገኖቻችንን ምንም አይነት ጥቃትም ይሁን ሌሎች ነገሮች እንዳይደርስባቸው ጥበቃ ልናደርግ ይገባል።

አንዳንድ አካላት ኃይማኖታዊ ሁከትና ብጥብጥ እንዲነሳ እየሰሩ በመሆኑ እያንዳንዱ ኢትዮጲያዊ ሙስሊም ለሀገር ሠላምና መረጋጋት ሲል የራሱን ደህንነት እንዲጠበቅ፣ ሁከትና ብጥብጥ ከሚፈጥሩ ጉዳዮች እንዲርቅ፣ ከሌሎች ኃይማኖት ተከታይ ወገኖቻችን ጋር እጅ ለእጅ ተያይዞ አጥፊዎችን እንዲያወግዝና መንግስት ጥፋተኞች ለሕግ እንዲያቀርብ በሰከነ ሁኔታ እንዲያግዝ አበክረን እንጠይቃለን።

ኃይማኖታችን አንዱ ባጠፋው ሌላውን የሚቀጣና እርምጃ የሚወስድ አቅጣጫ የሚያስቀምጥ ባለመሆኑ ሁላችንም ሙስሊሞች እንድንረጋጋ በአሏህ ስም እንጠይቃለን።

በጎንደር በአክራሪዎች ሕይወታቸው ለተቀጠፉ ሙስሊም ወንድሞቻችን አሏህ(ሱ.ወ) ማረፊያቸውን ጀነተልፊርዶውስ እንዲሰጣቸው እንለምነዋለን። አሏህ ሆይ! ማራቸው፤ ማረን

ሠላም፣ ፍቅር ፣ አንድነት ...ለሁላችንም!

https://t.me/ethio_muslim_nashida
https://t.me/ethio_muslim_nashida