Get Mystery Box with random crypto!

ከፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት በኋላ በትግራይ ክልል ከትምህርት አንጻር በርካታ ስራዎች መስራታቸው | Ministry of Education Ethiopia

ከፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት በኋላ በትግራይ ክልል ከትምህርት አንጻር በርካታ ስራዎች መስራታቸው ተገለጸ
.............................................................
ጥር 28/2016 ዓ.ም (ትምህርት ሚኒስቴር) የፌዴራል መንግስት እና የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ካደረጉት የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት በኋላ በትግራይ ክልል ከትምህርት አንጻር በርካታ ስራዎች መስራታቸውን ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ (ፒኤችዲ)  ተናግረዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህንን  የተናገሩት በ16ኛው የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 3ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 14ኛ መደበኛ ስብሰባ ለተጠየቁ ጥያቄዎች ምላሽ በሰጡበት ወቅት ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ከፕሪቶሪያው ስምምነት በፊት ትግራይ ውስጥ ትምህርት መቋረጡን ገልጸው አሁን ሁሉም ዩኒቨርስቲዎችና ከሞላ ጎደል ሁሉም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ስራ ጀምረዋል ብለዋል።

ይህንንም ለማሳካት የፌዴራል መንግስት፣ ትምህርት ሚኒስቴርና የክልሉ ትምህርት ቢሮ በትብብር በርካታ ስራ መስራታቸውን አስታውሰዋል።

በትምህርት ጥራት፣  መስፋፋት፣ በመጽሀፍት አቅርቦት እንደማንኛውም አካባቢ ክፍተት ሊኖር እንደሚችል የጠቆሙት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባጠቃላይ ግን  ትምህርት መጀመሩ አስደሳች መሆኑን ገልፀዋል።

በትግራይ ክልል በአራቱም ዩኒቨርስቲዎች ትምህርት እየተሰጠ ሲሆን በሁለተኛ ደረጃ  ትምህርት የ2015 ዓ.ም ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተናም መሰጠቱ ይታወሳል።