Get Mystery Box with random crypto!

የኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር ከኮሪያ ጋር በትምህርት ኢንፎርሜሽን ልውውጥና ትብብር ላይ የስምምነት | Ministry of Education Ethiopia

የኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር ከኮሪያ ጋር በትምህርት ኢንፎርሜሽን ልውውጥና ትብብር ላይ የስምምነት ሰነድ ተፈራረመ ፡፡
..................................... // ...............................
ጥር 2/2016 ዓ.ም (ትምህርት ሚኒስቴር) የኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር ከኮሪያ ጊዮንግሳንግቡክ-ዶ (Geongsangbuk-do) ትምህርት ቢሮ ጋር በትምህርት ኢንፎርሜሽን ልውውጥና ትብብር ዙሪያ በጋራ ለመስራት የሚያስችል የትብብር መግባቢያ ሰነድ ስምምነት ተፈራርሟል፡፡

የትብብር ስምምነቱ በሁለቱ ሃገራት መካከል ከ20016-2017 ዓ.ም የሚደረገውን የትምህርት ኢንፎርሜሽን ልውውጥና ትብብርን የተመለከተ ነው።
ስምምነቱ በሀገራቱ መካከል ያለውን የወዳጅነትና ድጋፍ ከማጠናከሩ ባሻገር በዲጂታል የትምህርት ስትራቴጂና የማስፈጸሚያ ዕቅድ አተገባበር እንዲዳብር ለማበረታታት ያስችላል ተብሏል፡፡

በትብብር ስምምነት ሰነዱ ላይ የአይሲቲ መሳሪያዎችን ማቅረብና ለተመረጡ መምህራን ከትምህርታዊ መረጃ አሰጣጥ ጋር የተያያዘ ስልጠና መስጠት የኮሪያ መንግስትን የሚመለከቱ መሆኑና የስልጠና ተሳታፊዎችን መምረጥን በተመለከተ የትምህርት ሚኒስቴርን የሚመለከቱ መሆናቸውን ተካተውበታል፡፡

የኢፌዲሪ ትምህርት ሚኒስቴር ሚንስትር ዴኤታ ወ/ሮ አየለች እሸቴ እና የጊዮንግሳንግቡክ-ዶ ቢሮ የትምህርት ዘርፍ አስተዳዳሪ ሊም ጆንግ-ሲክ በእለቱ ተገኝተው ስምምነቱን ፈርመዋል፡፡