Get Mystery Box with random crypto!

ብዝኃነትን መኖር በሚል መሪ ሐሳብ የአብሮነት ቀን ለስድስት ቀናት መከበር ጀምሯል። ......... | Ministry of Education Ethiopia

ብዝኃነትን መኖር በሚል መሪ ሐሳብ የአብሮነት ቀን ለስድስት ቀናት መከበር ጀምሯል።
.............................................
ታህሳስ 20/2016 ዓ.ም (ትምህርት ሚኒስቴር) እ.አ.አ. በ1995 የተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት ፦ ዩኔስኮ ኅዳር 6 ቀንን  ዓለም አቀፍ የአብሮነት (Tolerance) ቀን እንዲኾን ዐውጇል፡፡

የቀኑ መታወጅ ዓላማ በኅብረተሰቡ ውስጥ የአብሮነትን ጥቅም ግንዛቤ ለመፍጠርና መቻቻል ያለዉን ፋይዳ ማስገንዘብ ነው፡፡

በኢትዮጵያም ብዝኃነትን የሚያከብር፣ አብሮነትን ገንዘብ ያደረገ፣ ኃላፊነት የሚሰማዉ ትውልድ ለማፍራት የተጀመረዉን ጥረት ለማገዝ፣ ማኅበራዊ ዕሴቶቻችንን ለማሳደግና ለለውጥ ዝግጁ ዜጋና  ኅብረተሰብ ለመፍጠር ተቻችሎ መኖር አንዱ ለአንዱ አስፈላጊዉ አንደኾነ ማመንን ለማስረጽና ግንዛቤ ለማሳደግ ቀኑ ይከበራል፡፡ 

ዘንድሮ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ26ኛ ጊዜ በኢትዮጵያ ለ14ኛ ጊዜ የሚከበረዉ ዓለም አቀፉ የአብሮነት ቀን "ብዝኃነትን መኖር!" በሚል መሪ ሐሳብ ከታኅሣሥ 20-25 ቀን 2016 ዓ.ም እየተከበረ ይገኛል።

የአብሮነት ሳምንቱ በልዩ ልዩ ኹነቶች እንደሚከበር ከመርሐ ግብሩ መረዳት ተችሏል።

የበዓሉን አከባበር ባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ከተለያዩ የፌዴራል ተቋማትና ከሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጋር በመኾን ያስተባብራል።

ተጨማሪ መረጃዎችን በሚከተሉት ማስፈንጠሪያዎች ያግኙ፡-

በፌስቡክ -https://www.facebook.com/fdremoe/
በቴሌግራም -https://t.me/ethio_moe
በትዊተር - http://twitter.com/fdremoe
በሊንክዲን - https://www.linkedin.com/.../ministry-of-education-ethiopia
በዌብሳይት - www.moe.gov.et
ይከታተሉ