Get Mystery Box with random crypto!

በኦጋዴን ከ21 ቢሊዮን ሜትር ኪዩብ በላይ የተፈጥሮ ጋዝ መኖሩ ተረጋገጠ_ የማዕድን ሚኒስቴር በሶ | ETHIO-MEREJA®

በኦጋዴን ከ21 ቢሊዮን ሜትር ኪዩብ በላይ የተፈጥሮ ጋዝ መኖሩ ተረጋገጠ_ የማዕድን ሚኒስቴር

በሶማሌ ክልል ኦጋዴን 19 ጉድጓዶችን በመቆፈር በተደረገ ዳሰሳ "21 ቢሊዮን 336 ሚሊዮን ኩቢክ ሜትር የተፈጥሮ ጋዝ እንዳለ" መረጋገጡን የማዕድን ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የማዕድን ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሚሊዮን ማትዮስ፤ በሌሎች ስድስት ቦታዎች ላይም ነዳጅና የተፈጥሮ ጋዝ ሀብት መኖሩን ኢፕድ ተናግረዋል፡፡

#ኦጋዴን፣ #መቀሌ፣ #መተማ፣ #ደቡብ_ኦሞ እንዲሁም #ጋምቤላ አካባቢዎች በዋናነት ተጠቃሽ መሆናቸውንም አስገንዝበዋል፡፡

እንደ አቶ ሚሊዮን ገለጻ፤ በክልሉ የተገኘው የተፈጥሮ ጋዝ በቅርብ ዓመታት ወደ ምርት ለማስገባት ሰፋፊ ሥራዎች እየተሠሩ ነው፡፡ ሌሎች በፍለጋ ምዕራፍ ላይ ያሉትም በአጭር ጊዜ ውጤታማ የሚሆኑበት አቅጣጫ ተቀምጧል ብለዋል፡፡

     T.me/ethio_mereja
           ኢትዮ-መረጃ