Get Mystery Box with random crypto!

ጠ/ሚኒስትር አብይ በአማራ ክልል በአስቸጋሪ ሁኔታ የሚገኙ 6ሺ የሚጠጉ ሱዳናውያንን እንዲታደጉ ጥሪ | ETHIO-MEREJA®

ጠ/ሚኒስትር አብይ በአማራ ክልል በአስቸጋሪ ሁኔታ የሚገኙ 6ሺ የሚጠጉ ሱዳናውያንን እንዲታደጉ ጥሪ ቀረበላቸው!!

በአማራ ክልል “ከአውላላ የስደተኞች መጠለያ” ወጥተው በአቅራቢያው በሚገኝ መንገድ ዳር መኖር የጀመሩ ስድስት ሺ የሚሆኑ የሱዳናውያን ስደተኞች በአስቸጋሪ ሁኔታ ላይ በመሆናቸው እንዲታደጓቸው የሱዳን ድርጅቶች ለጠ/ሚኒስትር አብይ ጥሪ ማቅረባቸው ተገለጸ።

ከግንቦት ወር መባቻ ጀምሮ በአማራ ክልል ከሚገኙ የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች መጠለያ ካምፕ የጸጥታ ችግር አጋጥሞናል በሚል ካምፑን ለቀው በመውጣት በአቅራቢያቸው በሚገኝ ጫካ ውስጥ መኖር የጀመሩ ስድስት ሺ የሚጠጉ ሱዳናውያን መኖራቸውን ድርጅቶቹ ጠቁመዋል። ስድስት ሺ ከሚሆኑት እና በጫካው ውስጥ ከሚኖሩት ሱዳናውያኑ መካከል 2 ሺ 133 የሚሆናት ህጻናት መሆናቸውን የጠቆሙት ድርጅቶቹ 1 ሺ 17 የሚሆኑት ሴቶች፣ 1 ሺ 917 ወንዶች፣ 1 ሺ 135 የሚሆኑ በሽተኞች እና 76 የሚሆኑት ደግሞ ልዩ ድጋፍ የሚሹ ናቸው ብለዋል።

     T.me/ethio_mereja
           ኢትዮ-መረጃ