Get Mystery Box with random crypto!

ጊፍት ሪል ስቴት ከመንግስት ጋር በአጋርነት 2 ሺህ ቤቶችን በ3 ዓመታት ውስጥ ለመገንባት ስምምነት | ETHIO-MEREJA®

ጊፍት ሪል ስቴት ከመንግስት ጋር በአጋርነት 2 ሺህ ቤቶችን በ3 ዓመታት ውስጥ ለመገንባት ስምምነት ተፈራረመ

የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በተገኙበት ጊፍት ሪል ስቴት ከመንግስት ጋር የሚሰራዉን የቤቶች ፕሮጀክት ግንባታ በይፋ አስጀመረ።

በዚህ መርሃ ግብር ጊፍት ሪል ስቴት በዋና ከተማዋ ለገሃር አካባቢ በመጀመሪያ ዙር ግንባታ 4 ሺህ ቤቶችን መስራት መጀመሩ ተገልጿል። በሪል ስቴቱ የለገሃር መኖሪያ መንደር አነስተኛ እና መካከለኛ ገቢ ያላቸው የህብረተሰብ አካላትን በተመጣጣኝ ዋጋ ተደራሽ እንደሚያደርግ ጊፍት ሪል ስቴት አስታወቋል።

የዚህ የጊፍት ሪል ስቴት የለገሀር የመኖሪያ መንደር ፕሮጀክት ግንባታ በ3 ዓመታት ውስጥ የሚጠናቀቅ ሲሆን 3 ሺህ 540 የመኖሪያ እንዲሁም 460 የንግድ ቤቶች እንደሚኖሩት ተገልጿል። የመኖሪያ መንደሩ ትምህርት ቤት እና ሌሎች ማህበራዊና ማህበረሰባዊ መገልገያዎችን ያካተተ እንደሚሆን የተገለጸ ሲሆን የሕንጻዎቹ ከፍታ ከ14 እስከ 22 ወለል ይሆናል ተብሏል።

በሁለተኛ ዙር ለሚገነቡ 8 ሺህ የመኖሪያና የንግድ ቤቶች ግንባታ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑም ተመላክቷል።

     T.me/ethio_mereja
       @ethio_mereja