Get Mystery Box with random crypto!

ከማለዳው 11:00 ሰዓት ጀምሮ መንገዶቹ ለተሽከርካሪ ዝግ ናቸው የ2016 የኢትዮጵያ ታምርት የጎ | ETHIO-MEREJA®

ከማለዳው 11:00 ሰዓት ጀምሮ መንገዶቹ ለተሽከርካሪ ዝግ ናቸው

የ2016 የኢትዮጵያ ታምርት የጎዳና ላይ ሩጫ በአዲስ አበባ ይካሄዳል፡፡ ሩጫው ስኬታማ ሆኖ እንዲጠናቀቅ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት ማድረጉን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡
    
በውድድሩ ወቅት የተወሰኑ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚሆኑም ተገልጿል፡፡

ሚያዚያ 13 ቀን 2016 ዓ/ም  መነሻና መድረሻውን መስቀል አደባባይ ያደረገውና የአዲስ አበባን ዋና ዋና መንገዶችን የሚያካልለው የ2016 የኢትዮጵያ ታምርት የጎዳና ላይ የ10 ኪሎ ሜትር የሩጫ ውድድር በአዲስ አበባ ይካሄዳል፡፡

ከዚህ ቀደም በርካታ ህዝብ በብዛት የተሳተፈባቸው ተመሳሳይ  ሩጫዎች በሰላም መጠናቀቃቸውን ያስታወሰው ፖሊስ በመጪው እሁድ  በከተማችን የሚካሔደው የሩጫ ውድድር በሰላም እንዲጠናቀቅ የፀጥታ አካላት ዝግጅታቸውን አጠናቀው ወደ ስራ መግባታቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡ 

የሩጫው ተሳታፊዎች ፀጥታው የጋራ ጉዳይ መሆኑን ተገንዝበው ወደ መሮጫ ስፍራ ሲገቡ ለፍተሻ እንዲተባበሩ የአዲስ አበባ ፖሊስ  ጥሪውን አስተላልፏል፡፡

መነሻውን ከመስቀል አደባባይ በማድረግ   በለገሃር ፣ ሜክሲኮ አደባባይ ፣ ቡልጋሪያ ማዞሪያ ፣ ቄራ ፣ ጎተራ ማሳለጫ ፣ አጎና ሲኒማ ፣ ጥላሁን አደባባይ አድርጎ  መዳረሻውን መስቀል አደባባይ ያደረገው ውድድር  ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ
•  ከመገናኛ ወደ መስቀል የሚወስደው መንገድ ኡራኤል አደባባይ
•  ⁠ከኦሎምፒያ አደባባይ ወደ መስቀል
•  ⁠ከመስቀል ፍላዎር አደባባይ ወደ አጎና መስቀለኛ
•  ⁠ከጎርጎሪዎስ አደባባይ ወደ ጎተራ
•  ⁠ከጎተራ ሼል ወደ ጎተራ
• ⁠ከማሞ ማቋረጫ ወደ ጎተራ
•  ⁠ከጎፋ ገብርኤል ወደ ጎፋ ማዞሪያ
•  ⁠ከአልማዝዬ ሜዳ ወደ ቄራ በረት
•  ⁠ከመካኒሳ አቦ አደባባይ ወደ ሳር ቤት አደባባይ
•  ⁠ከካርል አደባባይ ወደ ሳር ቤት አደባባይ
•  ⁠ከልደታ ፀበል ወደ ኤዩ መብራት
•  ⁠ከቡልጋሪያ ማዞሪያ ወደኤዩ መብራት
•  ⁠ከኦርቢስ መታጠፊያ/ጮራጋዝ/ መስቀለኛ ወደ ሲጋራ ፋብርካ
•  ⁠ከጠማማ ፎቅ ወደ ጥይት ፋብርካ
•  ⁠ከላንድ ማርክ ሆስፒታል ወደ ገነት መብራት
•  ⁠ከከፍተኛ ፍ/ቤት /ባልቻ ሆስፒታል/ ወደ ሜክሲኮ አደባባይ
•  ⁠ከአረቄ ፋብርካ ወደ ሜክሲኮ አደባባይ
•  ⁠ከሠንጋ ተራ 40/60 መስቀለኛ ወደ ሠንጋ ተራ መብራት
•  ⁠ከበድሉ ህንፃ ወደ ቴሌ ባር
•  ⁠ከብሔራዊ ቲያትር መብራት ወደ ለገሃር መብራት
•  ⁠ከሀራምቤ መብራት ወደ ሳንጆሴፍ መብራት
•  ⁠ከብ/ቤተመንግስት ወደ መስቀል አደባባይ
•  ⁠ከኢንተርኮንትኔታል ሆቴል ወደ ባምቢስ የሚወስዱ መንገዶች ከማለዳው 11:00 ሰዓት ጀምሮ መንገዶቹ ለተሽከርካሪ ዝግ  እንደሚሆኑ እና ከዋዜማው ጀምሮ እስከ ውድድሩ ፍፃሜ ድረስ ጎፋ ማዞሪያ ድልድይ ፣ በቅሎ ቤት ድልድይ እና ጥላሁን አደባባይ ድልድይ አካባቢ ለረዥም ሆነ ለአጭር ጊዜ ተሽከርካሪ አቁሞ መሄድ ፍጽም የተከለከለ መሆኑን የአዲስ አበባ ፓሊስ አስታውቋል፡፡  በየአካባቢው ለተመደቡ የትራፊክ ፖሊስ እና የፀጥታ አካላት ተባባሪ በመሆን የሚሰጡትን ትዕዛዝ አሽከርካሪዎች  በማክበር የተለመደ ትብብራቸውን እንዲያደርጉ አዲስ አበባ ፖሊስ መልዕክቱን አስተላልፏል፡

     T.me/ethio_mereja
       @ethio_mereja