Get Mystery Box with random crypto!

ቪዲዮ:- አየር ላይ ሊሰራ የታሰበው ተንጠልጣዩ ሕንፃ! ህንፃው ከኅዋ ወደ ምድር ይገነባል የተባ | ETHIO-MEREJA®

ቪዲዮ:- አየር ላይ ሊሰራ የታሰበው ተንጠልጣዩ ሕንፃ!

ህንፃው ከኅዋ ወደ ምድር ይገነባል የተባለ ሲሆን የበርካታ አስደናቂ ህንፃዎች ባለቤት በሆነችው ዱባይ እንደሚገነባም ተነግሯል።

ቁመቱም 32000ሜትር ይሆናል የተባለለት ይህ ህንፃ በክላውድስ አርትቴክትስ ንድፉ እንደወጣለትም ተገልጿል።

ከህዋ ላይ የህንፃው መሰረት እንደሚሰራ የተነገረለት ይህ ህንፃ ከአስትሮይድ ጋር እጅግ ጠንካራ ከሆነ ኬብል ጋር በማያያዝ ቁልቁል ወደ መሬት ይወርዳል ተብሏል።

የሀይል ምንጩንም ህዋን መሰረት ያደረገ የሶላር ሲስተም ጋር እንደሚያገኝ የተነገረ ሲሆን ዉሀ ደግሞ ከዳመና ላይ በመሰብሰብ ይጠቀማል።በህንፃ ላይ ሰዎች እንዴት መውጣት እንደሚቻል ግልፅ ባያደርጉም፣ ከህንፃው መውረድ የፈለገ ሰው ግን ፓራሹት ይጠቀማል ተብሏል። የዚህ ህንፃ እውን መሆን ግን ብዙዎችን አጠራጥሯል።(ምንጭ፣ሀገሬ ቲቪ)

   - ETHIO-MEREJA -
   T.me/ethio_mereja