Get Mystery Box with random crypto!

ኬንያ በኢትዮጵያ እና በሶማሊያ መካከል ያለውን ውጥረት ለማርገብ ቀጠናዊ የባህር ስምምነት ሃሳብ አ | ETHIO-MEREJA®

ኬንያ በኢትዮጵያ እና በሶማሊያ መካከል ያለውን ውጥረት ለማርገብ ቀጠናዊ የባህር ስምምነት ሃሳብ አቀረበች!

ኬንያ በኢትዮጵያ እና በሶማሊያ መካከል ያለውን ውጥረት ለማርገብ ቀጠናዊ የባህር ላይ ስምምነት ሃሳብ ማቅረቧን ሮይተርስ የዜና ምንጭ ዘግቧል።

ኬንያ ፤ከጅቡቲ እና ከምሥራቅ አፍሪካ የልማት በየነ መንግሥታት ድርጅት ኢጋድ ጋር በመመካከር ያቀረበችው ይህ ስምምነት ወደብ የሌላቸው ሀገራት በንግድ እንዴት ወደብ መጠቀም እንደሚችሉ የሚገዛ መሆኑን የኬንያ የውጭ ጉዳይ ዋና ጸሃፊ ኮሪር ሲንግኦኢ ለሮይተርስ ተናግረዋል።የቀጠናው ሀገራትን የሚያገናኘው ኢጋድ የባህር ሃብትን ለመጋራት የሚያስችል ስምምነት መፍጠር እንደሚችልም የኬንያው የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ተናግረዋል።

የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሀሙድ በትናትናው ዕለት ከኬንያ አቻቸው ዊሊያም ሩቶ ጋር በኬንያ ዋና ከተማ ለውዝግቡ ዲፕሎማሲያዊ መፍትሄ ለማምጣት በሚደረገው ጥረት ተወያይተዋል።በውይይቱ መጨረሻም « ቀጠናው የተረጋጋ እንዲሆን ለማድረግ ከሁሉም አካላት ጋር መገናኘታችንን እንቀጥላለን» ሲሉ ሲንግኦይ መናገራቸውን የሮይተርስ ዘገባ ያሳያል።የናይሮቢ መፍትሄ ተቀባይነት ካገኘ ኢትዮጵያ «የተረጋጋ እና ተገማች የባህር ሀብት ተደራሽነት»ን ስለሚሰጥ የንግድ ስራዋን ያለምንም እንቅፋት እንድትፈጽም እና የሶማሊያን የግዛት አንድነት እንደሚያከብርም አክለዋል።

እንደ ሮፕተርስ ዘገባ ሶማሊያ እና ኢትዮጵያ ሃሳቡን እያጤኑበት ነው ያሉት ዳይሬክተሩ፥ መሪዎቻቸው ሂደቱን ወደፊት ለማራመድ ተገናኝተው እንዲመክሩበት ተጠይቀዋል።
.