በአዲስአበባ የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ የሚዲ-ባስ እና ሚኒ-ባስ ተሸከርካሪዎች የታሪፍ ማሻሻያ ይፋ ሊደረግ ነው!! በመዲናዋ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ የሚዲ-ባስ እና ሚኒ-ባስ ተሽከርካሪዎች አዲስ የታሪፍ ማሻሻያ ይፋ ሊደረግ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራንስፖርት ቢሮ አስታውቋል፡፡ ለህብረተሰቡ የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ የሚዲ-ባስና ሚኒ-ባስ ተሽከርካሪዎች አዲስ የትራንስፖርት ታሪፍ ማሻሻያ ነገ እለተ ማክሰኞ ከቀኑ 8፡30 ላይ ለሚዲያ ተቋማት ይፋ እንደሚደረግ ተገልጿል፡፡ የታሪፍ ማሻሻያው ከሰኔ 01 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረግ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን አፈፃፀሙ በተገቢው እንዲከወን የህግ አስከባሪ አካላት ሚና የጎላ በመሆኑ የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ ቢሮው አሳስቧል፡፡ህብረተሰቡም የሚወጣውን ትክክለኛ ታሪፍ አውቆ በመክፈልና ከታሪፍ በላይ የሚያስከፍሉ አሽከርካሪዎችን በማጋለጥ በኩል ጥቆማ በመስጠት የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ ቢሮው መልዕክት አስተላልፏል፡፡ T.me/ethio_mereja 21.7K viewsedited 12:49