Get Mystery Box with random crypto!

በአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በማላዊ አቻው ተሸነፈ!! የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድ | ETHIO-MEREJA®

በአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በማላዊ አቻው ተሸነፈ!!

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በኮቲዲቯር አስተናጋጅነት በሚካሄደው የአፍሪካ ዋንጫ የመጀመሪያውን የማጣሪያ ጨዋታ ከማላዊ አቻው ጋር ተጫውቷል። ይህ የማጣሪያ በማላዊ መዲና ቢንጉ ብሄራዊ ስታዲየም ተካሂዶ ዋሊያዎቹ ከ ማላዊ ጋር ያደረገውን ጨዋታ 2 - 1 በሆነ ውጤት ተሸንፏል።

የማላዊውን የማሸነፊያ ሁለት ግቦች ጋባዲንሆ ምህንጎ አስቆጥሯል። የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድንን ከሽንፈት ያልታደገችውን ግብ የኢትዮጵያ ቡናው አጥቂ አቡበከር ናስር አስቆጥሯል።

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ለመጨረሻ ጊዜ ያደረጓቸውን አስራ ሁለት የሜዳቸው ውጪ ጨዋታዎችን ማሸነፍ አልቻሉም።ዋልያዎቹ የዛሬውን ውጤት ተከትሎ ያለ ምንም ነጥብ የምድብ አራት መጨረሻ ደረጃን ያዘዋል።

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን የፊታችን ሀሙስ ምሽት 1:00 ከግብፅ አቻው ጋር ሁለተኛ የማጣሪያ ጨዋታቸውን እንደሚያከናውኑ የካፍ ድረገጽ የጨዋታ መርሃ ግብር ያስረዳል።
T.me/ethio_mereja