Get Mystery Box with random crypto!

የሰቆጣ ከተማ አስተዳደር የጸጥታ ም/ቤት ከከተማው ወቅታዊ ሁኔታ ተከትሎ የከተማውን ጸጥታና ሰላም | ETHIO-MEREJA®

የሰቆጣ ከተማ አስተዳደር የጸጥታ ም/ቤት ከከተማው ወቅታዊ ሁኔታ ተከትሎ የከተማውን ጸጥታና ሰላም ለማስከበር የተሰጠ መግለጫ

1.የትኛውም ተሽከርካሪ ከተፈቀደለትና ስምሪት ከተሰጠው ውጭ ከምሽቱ 1 ሰዓት እስከ ንጋቱ 11:30 መንቀሳቀስ የተከለከለ ነው።

2. ማንኛውም ግለሰብ ከምሽቱ 3:00 ሰዓት በኋላና ከንጋቱ 11:30 በፊት ከተፈቀደለት አካል ውጭ መንቀሳቀስ የተከለከለ ነው።

3.ማንኛውም የጦር መሳሪያ ስምሪት ከተፈቀደለት የጸጥታ አካል ውጭ ማንኛውም ግለሰብ የጦር መሳርያ ይዞ መንቀሳቀስ የተከለከለ ነው።

4.የጸጥታ መዋቅሩ በሚያከናውኗቸው ህግን የማስከበር ስራዎች ተባባሪ የማይሆን ለማደናቀፍ የሚሞክር ማንኛውም ግለሰብ አስፈላጊውን ህጋዊ እርምጃ የምንወስድ መሆኑን እናሳውቃለን።

5.ከከተማ አስተዳደሩ የጸጥታ አካላት ውጭ የመንግስትም ሆነ የግል ታጣቂዎች በከተማዋ የጦር መሳርያ ይዞ መንቀሳቀስ የተከለከለ ነው።

6.መጠጥ ቤቶች፣ግሮ ሰሪዎች የትኛውም የመዝናኛ ድርጅት ከምሽቱ 3:00 ሰዓት በኋላ አገልግሎት መስጠት የተከለከለ ነው።ሲሰጥ የተገኘ ድርጅት አስፈላጊውን ህጋዊ እርምጃ የሚወስድ መሆኑ።

7.በከተማችን በ4ቱ ቀበሌ በህገወጥ የመሬት ወረራ የተሳተፉ እስከ 12/09/2014 ዓ/ም ድረስ እራሳችሁ አፍርሳችሁ እንድትቆዩ።የማያፈርስ ካለ ህጋዊ እርምጃ በጸጥታ መዋቅሩ የሚወሰድበት መሆኑ።

8.የማህበራዊ ሚድያ ተጠቃሚዎች ሃሰተኛ መረጃ ማሰራጨት፣የግለሰቦችን ሰብዕና የሚያጎድፍ እንዲሁም ውድ ሂወቱ እየገበረ ላለው የጸጥታ መዋቅሩን ስም ማጠልሸት የተከለከለ ነው።

9.ከተማ አስተዳደሩ የህገወጥ ንግድን ለማስቆም እያደረገ ባለው ተግባር እንቅስቃሴ ውን ለመግታት ያልተገባ እቅስቃሴ ማድረግ የተከለከለ ነው።

10.ህገ ወጥ የገንዘብ ዝውውር ማድረግ በጥብቅ የተከለከለ ነው።

ኢትዮመረጃ - ሼር