Get Mystery Box with random crypto!

ትሕነግ የጦርነት ነጋሪት እየጎሰመ በመሆኑ በየደረጃው ያለው የፀጥታ መዋቅር ዝግጁ እንዲሆን የአማራ | ETHIO-MEREJA®

ትሕነግ የጦርነት ነጋሪት እየጎሰመ በመሆኑ በየደረጃው ያለው የፀጥታ መዋቅር ዝግጁ እንዲሆን የአማራ ክልል መንግሥት አሳሰበ!!

ወራሪው የትሕነግ ቡድን በየቀኑ የጦርነት ነጋሪት እየጎሰመ እና የትግራይን ሕዝብ ለጦርነት እያነሳሳ መሆኑን የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የጸጥታ ምክር ቤት አስታውቋል፡፡

የክልሉ የፀጥታ ምክር ቤት ባደረገው ስብሰባ የክልሉን ሰላምና ፀጥታ ሁኔታ በዝርዝር የገመገመ ሲሆን የአሸባሪው ትሕነግን አደገኛ ቅዠት መመከትና መቀልበስ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ተወያይቷል፡፡ ምክር ቤቱ በየደረጃው ያለው የፀጥታ መዋቅር ዝግጁ መሆን እንዳለበትም አቅጣጫ ያስቀመጠም ሲሆን በጉዳዩ ላይ መግለጫ አውጥቷል፡፡

በአንድ በኩል ከፌደራል የጸጥታ መዋቅር ጋር በመቀናጀት ከወያኔ የሚሰነዘርብንን ጥቃት ለመከላከል በተጠንቀቅና በዝግጁነት መቆም፤ በሌላ በኩል ደግሞ በውስጣችን ለወያኔ ሴራ ምቹ ሁኔታ የሚፈጥሩትን ህገ-ወጦችንና ስርዓት አልበኞችን በመቆጣጠር የክልላችን ሰላምና ደህንነት ማስጠበቅ ግንባር ቀደም የትኩረት አቅጣጫ እንዲሆኑ የክልሉ የፀጥታ ምክር ቤት ወስኗል።

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የፀጥታ ምክር ቤት የሰጠው መግለጫ ሙሉ ቃል አንደሚከተለው ቀርቧል፡-
https://telegra.ph/የአማራ-ክልል-ሙሉ-መግለጫ-05-13

T.me/ethio_mereja
ኢትዮ-መረጃ