Get Mystery Box with random crypto!

የህውሓት ቡድን የመጨረሻ ምዕራፍ ላለው ጦርነት የትግራይ ህዝብ እንዲዘጋጁ ጥሪ አቀረበ የአማፂው | ETHIO-MEREJA®

የህውሓት ቡድን የመጨረሻ ምዕራፍ ላለው ጦርነት የትግራይ ህዝብ እንዲዘጋጁ ጥሪ አቀረበ

የአማፂው የህውሓት ቡድን መሪ ደብረፅዮን ገብረሚካዔል ከመንግስት ጋር ችግሮችን በዲፕሎማሲ ለመፍታት ሲደረግ የነበረው ጥረት ባለመሳካቱ የትግራይን ሕዝብ ነፃነት ለማረጋገጥ የክልሉ ህዝብ እንዲዘጋጅ ጥሪ አቀረቡ።

የትግራይ ህዝብ አሁን ያለበት የከፋ ስቃይ እንዲቀለበስና የትግራይ የራስን ዕድል በራስ የመወሰን መብት እንዲረጋገጥ ለማድረግ የመጨረሻው ምዕራፍ ላይ ደርሰናል ማለታቸውን ዋዜማ ሬዲዮ ዘግቧል።

ፈትለወርቅ ገብረእግዚአብሄር(ሞንጀሪኖ)፣ አለም ገብረሐዋድና ጌታቸው ረዳን ጨምሮ የሕወሓት ከፍተኛ አመራሮች በተለያዩ የትግራይ አካባቢዎች ነዋሪዎችን ያወያዩ ሲሆን ሕዝቡ ለመጨረሻው ምዕራፍ ትግል እንዲዘጋጅ ጠይቀዋል።

በአለም አቀፉ ማህበረሰብ አሸማጋይነት ጊዚያዊ ስምምነት ተደርጎ ወደ ክልሉ እህል መድሀኒትና ሌሎች ድጋፎች እንዲገቡ ጥረት ብናደርግም እስከ አሁን ድረስ የተገኘው ድጋፍ ችግሩን ለማቃለል በቂ አይደለም ብለዋል።

መላክ ያለበትን መልዕክት ለሚመለከታቸው አካላት ሁሉ ባለን የመገናኛ መንገድ አድርሰናል ያሉት ደብረፅዮን የሚመለከታቸው ያሏቸውን አካላት አልዘረዘሩም። መንግስት የእርዳታ እህሎችን እንዳይደርስ ሕወሓት እንዳስተጓጎለ ተናግሯል ነገር ግን እርዳታ እንዲገባ አመቻችተን በቅርቡ ይዘነው ከነበረው የአፋር ክልል ሙሉ በሙሉ ለቀን ወተናል ሲሉ ተናግረዋል።

ምንጭ፦ ዋዜማ ሬድዮ
T.me/ethio_mereja
ኢትዮ-መረጃ