Get Mystery Box with random crypto!

❖ ዩቲዩብን እንዴት የገቢ ምንጭ ማድረግ ይችላሉ? ▄▄▄▄▄▄▄▄▄▄▄▄▄▄▄ ❑ ዩቲዩብ ለብዙ | ኢትዮ ኢንፎቴክ (Ethio Infotech)

❖ ዩቲዩብን እንዴት የገቢ ምንጭ ማድረግ ይችላሉ?
▄▄▄▄▄▄▄▄▄▄▄▄▄▄▄

❑ ዩቲዩብ ለብዙዎቻችን ተንቀሳቃሽ ምስሎችን በነፃ የምንኮመኩምበት ድረ-ገፅ ነው።

ነገር ግን ዩቲዩብ ከዚህም አልፎ ለብዙዎች የገቢ ምንጭ መሆን ከጀመረ ሰነባብቷል፤ ታዋቂነት ከማትረፍም በላይ ሚሊዬነር መሆን የቻሉ ጥቂት አይደሉም።

አብዛኛው ተጠቃሚ በነፃ ከሚመለከተው ተንቀሳቃሽ ምስል እንዴት ገቢ ሊገኝ ይችላል? የሚለው ግን የብዙዎች ጥያቄ ነው። እነሆ አምስት መንገዶች...

①• ማስታወቂያዎች
╤╤╤╤╤╤╤╤╤

❑ የመጀመሪያው ዩቲዩብን የገቢ ምንጭ ማድረጊያው መንገድ ማስታወቂያ ነው። አንድ ምስል ከመመልከትዎ በፊት የሚመጣው ማስታወቂያ ለዩቲዩበኞች አንደኛው የገቢ ምንጫቸው ነው።

አንድ ሺህ ተጠቃሚዎች ማስታወቂያውን በተመለከቱ ቁጥር ጉግል ለዩቲዩበኛው ከ1 ዶላር 5 ዶላር ድረስ ሊከፍል ይችላል።

ነገር ግን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ዩቲዩብ 50 በመቶውን ገቢ መውሰድ በመጀመሩ ምክንያት ከማስታወቂያ የሚገኘው ገቢ እጅግ ቀንሷል።

እርስዎ አንድ ምስል ዩቲዩብ ላይ ሰቅለው የእርስዎን ምስል ለማየት የሚመጡ አንድ ሚሊዮን ሰዎች ማስታወቂያውን ከተመለከቱ ከ1ሺህ ጀምሮ እስከ 5ሺህ ዶላር ሊያገኙ ይችላሉ ማለት ነው።

②• ለሚከፍሉ/ለሚለግሱ ማሳየት
╤╤╤╤╤╤╤╤╤╤

❑ ዩቲየበኞች ሰው ብዙም የማያውቀው የገንዘብ መሰብሰቢያ መንገድ በመጠቀምም ገቢ ያገኛሉ።

ታዋቂው እንግሊዛዊ ዩቲዩበኛ ኢቫን ኤዲንገር እንደሚናገረው "በይነ-መረብን በመጠቀም ሳንቲም ማሰባሰብ የሚቻልበት መንገድ እንደሆነ አስቡት" ይላል።

"ተጠቃሚዎች ቪዲዎችን ተመልክተው ከወደዷቸው ከ1 ዶላር ጀምሮ በወር እርዳታ እንዲለግሱ የሚያደርግ ሂደት ነው" ሲል ይተንትናል።

አንዳንድ ዩቲዩበኞች መሰል ሂደት ያለውን ጥቅም በመረዳት እርዳታ የሚለግሱ ተጠቃሚዎች ብቻ ምስሎቹን የሚመለከቱበት ድረ-ገፅ ይዘረጋሉ።

③• ተያያዥ ድረ-ገፆች
╤╤╤╤╤╤╤╤

❑ ይህ መላ በተለይ ፋሽንና የመዋቢያ ውጤቶችን በተመለከተ ተንቀሳቃሽ ምስል ሰርተው ዩቲዩብ ላይ ለሚሰቅሉ በጣም ተመራጭ ነው።

ለምሳሌ ዩቲዩበኞቹ አንድ የመዋቢያ ውጤት የሆነ የምርት ዓይነትን ጥቅምና ጉዳት ከተነተኑ በኋላ ያንን ምርት መሸመት የሚፈልጉ ሰዎች ተያይዞ በተቀመጠው ድረ-ገፅ አማካይነት ምርት መግዛት እንደሚችሉ ይጠቁማሉ።

በዚህ መንገድም የመዋቢያ ምርቱን ከሚሸጠው ድርጅት ጋር ባላቸው ስምምነት መሠረት ጥቅም ያገኛሉ ማለት ነው።

④• ምርት ጥቆማ
╤╤╤╤╤╤╤

❑ ፖስተሮች፣ ቲሸርት እንዲሁም የተንቀሳቃሽ ስልክ አካላት ዩቲዩበኞች ገቢ የሚያገኙባቸው ሌሎች መላዎች ናቸው።

ለምሳሌ አንዲት ዩቲዩበኛ በድረ-ገፁ በምታስተላልፈው መልዕክት ላይ አንድን ምርት የሚጠቁም ቲሸርት ለብሳ ወይም ስልክ ይዛ ብትታይ ይህ ማለት ተዘዋዋሪ ምርት ማስተዋወቅ በመሆኑ ሌላ የገቢ ምንጭ ሆኖ ያገልግላል።

የምርት ምልክት (ብራንድ) ነገር በዚህ ብቻ የሚያበቃ አይደለም።

⑤• የምርት ምልክት (ብራንድ) ማስታወቂያ
╤╤╤╤╤╤╤╤╤╤╤╤

❑ ኤዲንገር እንደሚናገረው የምርት ምልክት ለዩቲዩበኞች ዋነኛ የገቢ ማግኛ መላ ነው።

ብዙ ጊዜ ኩባንያዎችና አምራቾች ብዙ ተከታይ ባላቸው ዩቲዩበኞች አማካይነት ምርቶቻቸውን ያስተዋውቃሉ፤ ለዚህም በርካታ ገንዘብ ይከፍላሉ።

"ሉክ የተባለ ባልንጀራዬ ከአንድ የአሜሪካ ኩባንያ ጋር የ26 ሺህ ዶላር ስምምነት እንደተፈራረመ አውቃለሁ" ይላል ኤዲንገር።

ብዙ ተከታይ (ሰብስክራይበር) ያላቸው ዩቲዩበኞች ከላይ በተጠቀሱት መንገዶች የትየለሌ ትርፍ ሊያገኙ ይችላሉ፤ እያተረፉም ይገኛሉ።
══════❁✿❁ ══════
@ethio_computer_sciences