Get Mystery Box with random crypto!

ይህ ምስኪን መካኒክ ከዚች ቆንጆ ልጅ ጋር ኢንተርኔት ላይ ይገናኛሉ። አንድ ቀን ልጅቷ እሱ ጋር ለ | ኢትዮ ፈገግታ

ይህ ምስኪን መካኒክ ከዚች ቆንጆ ልጅ ጋር ኢንተርኔት ላይ ይገናኛሉ። አንድ ቀን ልጅቷ እሱ ጋር ለመምጣት የትራንስፖርት ገንዘብ እንዲልክላት ጠየቀችው።  ምስኪኑ መካኒክ ተገረመ።  ልጅቷ የምታታልለው መስሎት ነበር።

እንደዚች አይነት ቆንጆ ልጅ ወደ እሱ ልትመጣ እንደምትፈልግ ማመን አልቻለም። ግን ቢሆንም አመናት  ከሁለት ቀን በኋላ ከአለቃው ገንዘብ ተበድሮ ወደ ልጅቷ ላከ።  በጣም የሚገርመው ልጅቱ እሱን ለማየት ከአቡጃ ወደ ሌጎስ ናይጄሪያ በረረች። እሱ ግን ያላወቀው ይህች ቆንጆ ልጅ በጣም ሀብታም ከሆኑ ቤተሰብ የተገኘች እና እውነተኛ ፍቅር አሁንም እንዳለ እና ሁሉም ሴቶች የወንዶችን ገንዘብ እንደማይፈልጉ ለወንዶች እውነቱን ለማሳየት ፈልጋለች።

መጀመሪያ ሰውዬው ወደአላት አድራሻ ሄዳ ፍቅረኛዋ ባለ አንድ ክፍል አፓርትመንት ውስጥ ከሌሎች 7 ወንዶች ጋር እንደሚኖር አወቀች።  ፍቅረኛዋን የት እንደምታገኝ ጠይቃቸው መንገድ ላይ ስራ ላይ እንደሆነ ነገሯት። የሚሠራበት ቦታ ድረስ ሄዳ ሰርፕራይዝ ለማድረግ በራይድ ሄደች ። የሚሰራበት አካባቢ ስትደርስ መንገድ ላይ ልጁን እየጠየቀች መጣች እና ሰዎች 'ያ አስቀያሚ ልጅ በሰው መኪና ስር አንድ ቦታ ተኝቷል ሙሉ በሙሉ ልብሱ ቆሽሾ ያለው ' እያሉ ያሾፉባት ጀመር። 

ልጅቷ ፍለጋዋን ቀጠለች በመኪናቸው ውስጥ ያሉት ሀብታሞች ትኩረቷን ፈልገው ሲያፏጩም እሷ ግን በመጨረሻ የቆሸሸውን ልጅ ፍቅረኛዋን ከመኪና ጀርባ ተቀምጦ ስታገኘው እቅፍ አድርጋ ሮጣ ሄዳ ተጠመጠመችበት ልጁ ማልቀስ ጀመረ።

እናም እንዲህ አለ፡- ‘ከሟች እናቴ በስተቀር በአዋቂነት ህይወቴ በሙሉ ልታቅፈኝ ይቅርና እጄን ለመጨበጥ የተስማማች ሴት አንድም የለችም።  ሁለቱም ማልቀስ ጀመሩ።  በኋላ ልጅቷ ለ 5 ዓመታት በከተማ ውስጥ አፓርታማ ተከራይታ ለሥራው የሚጠቀምበት ሞተር ብስክሌት ገዛችለት፡፡ አሁን ሁለቱም ወደ ካናዳ ለመጓዝ አቅደው ዝግጅት ላይ ናቸው።

https://t.me/Ethio_fegegita
https://t.me/Ethio_fegegita