Get Mystery Box with random crypto!

ከአርባ በላይ የአማርኛ ፊልሞች ላይ የተወነው ተዋናይ ታሪኩ ብርሃኑ (ባባ) በድንገተኛ ህመም ዛሬ | Bekulu Entertainment

ከአርባ በላይ የአማርኛ ፊልሞች ላይ የተወነው ተዋናይ ታሪኩ ብርሃኑ (ባባ) በድንገተኛ ህመም ዛሬ ጠዋት አርፏል ።

ተዋናዩ ካባለቤቱ የፊልም ተዋናይት
ቃልኪዳን ጥበቡ ጋር ከተለያየ በኋላ ድብርት ተደጋግሞ ያጠቃው እንደነበር ፊደል ፖስት ከቅርብ ወዳጆቹ ሰምቷል።

ዕድሜው በሰላሳዎቹ አጋማሽ የሚገኘው ተዋናይ ታሪኩ ተውልዶ ያደገው ተክለ ሐይማኖት አካባቢ ሲሆን የአንድ ልጅም አባት ነው።

በአጭር ጊዜ ውስጥ ዝናን አና በብዙዎች ተወዳጅነትን ያተረፈ ተዋናይ ነው። በጉዳዬ ፊልም ላይ ደግሞ በድርሰት ፣ በዳይሬክተርነት እንዲሁም በትወና ተሳትፎበታል።

ከተወነባቸው ፊልሞች መካከል :- 300ሺ፣ የፍቅር ABCD ፣ ብላቴና፣ ቦሌ ማነቂያ ፣ እንደ ባል እና ሚስት ፣ ኢንጂነሮቹ ፣ እርቅ ይሁን ፣ ኢዮሪካ ፣ ጉዳዬ ፣ ሀገርሽ ሀገሬ ፣ ሕይወቴ ፣ ህይወት እና ሳቅ ፣ ከባድ ሚዛን ፣ ፍቅር እና ፌስቡክ ፣ ከቃል በላይ፣ላውንድሪ ቦይ ፣ ኮከባችን ፣ ማርትሬዛ ፣ ይመችሽ-የአራዳ ልጅ 2 ፣ ሞኙ የአራዳ ልጅ ፣ ትዳርን ፍለጋ ፣ አንድ ሁለት ፣ ብር ርርር ፣ ወደው አይሰርቁ፣ ወፌ ቆመች፣ ወንድሜ ያዕቆብ ፣ እንደ ቀልድ ፣ ወቶ አደር፣ አባት ሀገር፣ የሞግዚቷ ልጆች፣ ይዋጣልን ፣ ዋሻው፣ ወሬ ነጋሪ ፣ ወጣት በ97 ተጠቃሽ ናቸዉ።

#የኔቲዩብ ለአርቲስቱ ቤተሰቦች፣ ወዳጅና አድናቂዎች መፅናናትን ይመኛል።

ለበለጠ መረጃና ጥቆማ በዚህ ላኩልን፡፡
@ethio27info_bot @ethio27info