Get Mystery Box with random crypto!

7 ተጨማሪ የፓስፖርት መቀበያ ቦታዎች ይፋ ሆኑ። የኢትዮጵያ ኢሚግሬሽን፣ ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ 7 | Ethiopian passport service

7 ተጨማሪ የፓስፖርት መቀበያ ቦታዎች ይፋ ሆኑ።

የኢትዮጵያ ኢሚግሬሽን፣ ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ 7 ተጨማሪ የፓስፖርት መቀበያ ቦታዎችን ዛሬ ይፋ አድርጓል።

ከዚህን ቀደም የፖስፖርት መቀበያ ቦታ ዋናው ፖስታ ቤት ብቻ እንደነበር አስታውሷል።

አገልግሎቱን ተደራሽ ለማድረግ ተጨማሪ ፓስፖርት መቀበያ ቦታዎች በማስፈለጋሸው 7 ተጨማሪ የመቀበያ ቦታዎች ይፋ ሆነዋል ብሏል።

ከታች በተዘረዘረው የስም መነሻ ፊደል መሠረት ፓስፖርት መቀበል እንደሚቻል ኤጀንሲው አሳውቋል።

- ዋናው ፖስታ ቤት ፊደል ፦ የስም መነሻ ፊደል፡ A, M, Q, R, S, X,Y,Z

- አራት ኪሎ ፖስታ ቤት :- የስም መነሻ ፊደል፡ E,F

- አራዳ ፖስታ ቤት :- የስም መነሻ ፊደል፡ B,C,D

- ልደታ ፖስታ ቤት :- የስም መነሻ ፊደል፡ G,H,I

- ሰንጋ ተራ ፖስታ ቤት :- የስም መነሻ ፊደል፡ J,K,L

- አፍሪካ ጎዳና(ደንበል) ፖስታ ቤት :- የስም መነሻ ፊደል፡ N,O,P

- ካዛንችስ ፖስታ ቤት :- የስም መነሻ ፊደል፡ T,U,V,W