Get Mystery Box with random crypto!

​​​​ ለፍቅሬ ስል እውነተኛ የፍቅር ታሪክ | ልብወለዶች፣ መፅሀፎች

​​​​ ለፍቅሬ ስል

እውነተኛ የፍቅር ታሪክ
❐ ክፍል 10 ❑​​​​



..ወንድሜን ደህንነቱን ከጠየኩት ቡሃላ ስለ እናቴ ጠየኩት ግን የነገረኝ ነገር ትንሽ ይከብዳል ..."እናታችን ታማለች ባለፈው የላክሽው ብር አባዬ ሳይሞት ለተበደርነው ተከፍሏል አሁን ግን እናታችን መታከምያ አጥታ እቤት ተኝታለች ለምንበላውም እራሱ እጅ አጥሮናል እኔም ትምህርት መሄድ ትቻለው" አለኝ ቅስሜ ተሰበረ ምናለ ለናቴ በላኩት ብሩን ብዬም ተፀፀትኩ ከ20 ቀን ቡሃላ ደሞዝ ተቀብዬ እንደምልክላቸው ነግሬው በለቅሶ ስልኩ ተዘጋ ...ለፍቅር ግን አልነገርኩትም ብቻዬን ቻልኩት መኖሬን ትርጉም የሚሰጠው የሚመስለኝ ፍቅር ብቻ ነው ሰሞኑን ግን እሱም የለም ምን እንደሆነ ሳይነግረኝ እንኳ ኦንላይን ከገባ ሳምንት ሆነው ይባስ ህመም ፈጠረብኝ የእናቴ ህመም የፍቅር ናፍቆት እንቅልፍ ነሳኝ መተከዝ መጨነቅ ማልቀስ ጀመርኩ ማዳሜ ግን ግድ የላትም ብቻ ስራዋ ይሰራላት ...ፍቅር በጠፋ በ18ኛ ቀኑ ፃፈልኝ ፊቴ በራ ለምን እንደጠፋ ስጠይቀው አሞት እንደሆነ ነገረኝ ደሞ የረሳሁት ፍቅር ከሴት ጋር እየሳመችው የተነሳውን ፎቶ ፕሮፋይሉን ስጎረጉር አግኝቼ ማናት ብለው የጓደኛው ፍቅረኛ እንደሆነች ነግሮኛል ስለማፈቅረው ምንም ቢል አምነዋለው። ፍቅር የሃኪም ቤት ብር እንደጎደለበትና እንድሰጠው እንደሚፈልግ በግልፅ ነገረኝ ደነገጥኩ ለእናቴ መላክ እንዳለብኝና እንደታመመች ነገርኩት ግን አኮረፈኝ ብፅፍለትም አይመልስ አሁን ልቤ ተከፈለ ደግሜ ላጣው እንደሆነ ተሰማኝ አፈቅረዋለሁ በጣም ...ድሮ ወንድ አውሬ በሚመስለኝ ግዜ ቢያንስ ማፍቀር እንደምችልና መፈቀር እንደምችል አሳይቶኛል ተንከባክቦኛል... እናቴ ደግሞ እናት ናት ለአባቴ ባልደርስ እንኳ እናቴን ማዳን ወንድሜን ማስተማር አለብኝ ግራ ገባኝ አለቀስኩ ያለኝ ምርጫም ማልቀስ ነበር ዛሬ ጠዋት ማዳሜ ብሩን ስትሰጠኝ አንድ ነገር ነገረችኝ እሱም በቅርብ አሜሪካ እንደሚሄዱ እኔን እናቷ ጋር እንደምታረገኝ ነገረችኝ... እኔም የግዜው ችግሬን እናቴንና ፍቅርን እያሰብኩ ነገ የምልከውን ብር ተቀብያት ክፍሌ ገባው፣ ግራ መጋባቴ አብሮኝ አደረ እንቅልፍ ለስሙ እንኳ ሳይዘኝ እንዳፈጠጥኩ ነጋ ...ተነስቼም የለት ስራዬን ጀመርኩ ደግነቱ እቤት ማንም ስለማይውል የተወሰነ ነፃነት ይሰማኛል... ሰአቱ ይሮጣል ፍቅር ግን የውሃ ሽታ ሆኖብኛል 'ምናለ ይቅርታ ባያረግልኝ፤ ምናለ ደግሜ ባላገኘው፤ ምናለ ኧረ ጭርሱን ባላቀው' ሁሉንም ደግሜ ሳስበው እንደአዲስ ሆድ ይብሰኝና ተንሰቅስቄ አለቅሳለሁ ...ፈጣሪ የሚወደኝ አይደለም ጭርሱን የሚያውቀኝ አልመስልሽ ብሎኛል ሁፍፍፍ ሁሌ በደልና ስቃይ ችግር የማያጣኝ ፍጡር ...ተመስገን የምልበት ቀን ናፈቀኝ ...አሁን ማዳሜ መጣች ከስራ ጠርታኝም ተመልሳ መውጣት እንደምትፈልግ ነግራኝ ብሩን እንድትልክልኝ ነግሬአት ስለነበር እንድሰጣት ጠየቀችኝ እኔም በእናቴና በፍቅር ልቤ ተከፍሎ ስጨነቅ ስለነበር ሳላስበው ድንጋጤ ወረረኝ ግን ለእናቴ አደላው ቢያንስ እናቴን ላድን ባይሆን ባያናግረኝም ለፍቅር የሚቀጥለውን እልክለታለው ምክንያቱም ፍቅር ጨካኝ ስላልሆነ ይቅርታ ያረግልኛል ብዬ ራሴን አፅናናሁት... ብሩን ለእናቴ በላኩ በሳምንቱ ስደውልላት ምርቃትዋ የደስታ እንባዋ ንግግሯ ብቻ ሁሉ ነገሯ ልብ ይነካ ነበር በቃ ውስጤ ሲረካ ተሰማኝ የእራስን ደስታ ለሰው መስጠት ለካ ደስ ይላል ...
.....ይቀጥላል

ቶሎ ቶሎ እንዲለቀቅ share ያድርጉ