Get Mystery Box with random crypto!

የሰሚት 40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች የመንገድ ግንባታ 81 በመቶ ደርሷል የአዲስ አበባ ከተማ መ | Ethiopian Construction Work Professionals - ETCONp

የሰሚት 40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች የመንገድ ግንባታ 81 በመቶ ደርሷል

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን የከተማዋን የመንገድ ሽፋን ለማሳደግና የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የመንገድ መሰረተ-ልማት ግንባታ ከሚያከናውንባቸው አካባቢዎች መካከል የጋራ መኖሪያ ቤቶች የተገነቡባቸው መንደሮች ይገኙበታል፡፡

ባለስልጣኑ ለጋራ መኖሪያ ቤቶች የግንባታ መፋጠን ከፍተኛ ድርሻ ያላቸው የመግቢያና መውጫ የአክሰስ መንገዶችን ከመገንባት ባለፈ፣ ለቤት ልማት ተጠቃሚዎች አገልግሎት የሚውሉ የውስጥ ለውስጥ እና ወደ ዋና ዋና መንገዶች የሚያደርሱ መጋቢ መንገዶችን በመገንባት ለአገልግሎት ሲያበቃ ቆይቷል፡፡

አሁን ላይ በከተማዋ ምስራቃዊ ክፍል የመንገድ መሰረተ-ልማት ግንባታ እየተከናወነባቸው ከሚገኙ አካባቢዎች መካከል የሰሚት 40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች መንደር አንዱ ነው፡፡

ከዚህ ቀደም ምንም ዓይነት የመንገድ መሰረት ልማት ባልነበረበት የሰሚት 40/60 ኮንዶሚኒየም እየተገነባ የሚገኘው የውስጥ ለውስጥ የአስፋልት መንገድ፣ ለጋራ መኖርያ ቤቶች ነዋሪዎች እና ለአካባቢው ማህበረሰብ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ እድገት ከፍተኛ ጠቀሜታ እንደሚሰጥ ይታመናል፡፡

ፕሮጀክቱ በአጠቃላይ 1 ኪሎ ሜትር ርዝመትና ከ8 እስከ 15 ሜትር የጎን ስፋት የሚሸፍን ነው፡፡ አሁን ላይ 800 ሜትር የሚሆነው የመንገዱ ክፍል አስፋልት የለበሰ ሲሆን፣ በቀሪው 200 ሜትር ላይ ደግሞ አስፋልት ለማልበስ የሚያስችሉ የግንባታ ስራ በመከናወን ላይ ይገኛል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን የራስ ኃይል እየተገነባ የሚገኘው የዚህ ፕሮጄክት የግንባታ ፊዚካል አፈፃፀም 81 በመቶ ላይ ደርሷል፡፡

አዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን

@etconp