Get Mystery Box with random crypto!

ግልጽነት የጎደለው የአሹራ ክፍያ ነገር•••           **** የአዲስ አበባ ግንባታና ቁጥጥር | Ethiopian Construction Work Professionals - ETCONp

ግልጽነት የጎደለው የአሹራ ክፍያ ነገር•••
          ****
የአዲስ አበባ ግንባታና ቁጥጥር ባለስልጣን በመመሪያ ቁጥር ግፈቁባ/9561/3014፣ በ2014 ዓ.ም. ባወጣው የግንባታ ዋጋ ክለሳ መሰረት:-

ለሁሉም የህንጻ ዐይነቶች የግንባታ ተመን፣

1. G+0 ቤት ብር 10,000/ካሬ ሜትር፣
2. ከG+1 በላይ ለንግድ፣ ለመኖሪያ እንዲሁም ለቅይጥ ህንጻዎች ብር 12,200/ካሬ ሜትር፣
3. ለሆስፒታል አገልግሎት የሚሆን ህንጻ ብር 20,000/ካሬ ሜትር ፣

በሚል የዋጋ ትመና አውጥቶ ሰዎች የንብረት ስም ዝውውር በሚፈጽሙ ጊዜ ለመንግስት የሚከፈለው የ2% የቴምብርና የ4% የአሹራ ክፍያ በእዚህ ዋጋ ላይ ሲሰላ ቆይቷል።

ይሁንና ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ አዲስ የከለሰው መመሪያ ለህዝብ ግልጽ ባልተደረገበት ሁኔታ በቅርቡ በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ ክፍለ ከተሞች ዜጎች የቤት ባለቤትነት ለማዘዋወር ጥያቄ ሲያቀርቡ  የቤቶች የግንባታ ዋጋ፣

1. G+0 ህንጻ ብር  20,000/ካሬ ሜትር፣
2. ከG+1 እስከ G+ 5 ህንጻ ብር 25,000/ካሬ ሜትር፣
3. ከG+6 እስከ G+ 10 ህንጻ ብር 30,000/ካሬ ሜትር፣
4. ከG+11 እስከ G+15 ህንጻ ብር 35,000/ካሬ ሜትር፣
5. ከG+15 ህንጻ በላይ ብር 40,000/ካሬ ሜትር፣

መሆኑን የሚገልጽ ነገር ተለጥፏል።

በየክፍለ ከተሞቹ ዜጎች ይሄንኑ አዲስ ወጣ የተባለ የዋጋ ትመና መሠረት ባደረገ መልኩ የአሹራ ክፍያ እየፈጸሙ ይገኛሉ።

መመሪያውን በተመለከተ...

1ኛ/የቤቱ ዓይነት ቅንጡ ህንጻም ይሁን እንደነገሩ የተገነባ ህንጻ ተመሳሳይ የግንባታ ዋጋ በካሬ ሜትር ማስቀመጡ፣

2ኛ/ኮንዶሚንየም የሚሸጡ ሰዎችን በተመለከተ መመሪያው ምንም ስለማይል ምድር ቤት ኮንዶሚንየም የሚሻሻጡ ሰዎች ዝቅተኛ አሹራ (20,000 በካሬ)፣ 6ኛ ፎቅ ላይ ያለ ቤት የሚሻሻጡ ሰዎች ከፍተኛ አሹራ (30,000 በካሬ) እንዲከፍሉ  ይገደዳሉ። ከእዚህ በተቃራኒ የቤት ሽያጭም ሆነ ኪራይ ዋጋ የሚወደደው ታች ባሉ ወለሎች ላይ መሆኑ እና መመርያው ይሄንን ከቁብ ያላስገባ መሆኑ፣

3ኛ/በቅርቡ ኢኮኖሚዬ hyperinflationary አይደለም (የሶስት አመት አጠቃላይ የግሽበት መጠኔ ከ100% አይበልጥም ) በማለት መግለጫ ያወጣ መንግስት፣ ዋነኛ የዋጋ ንረት መለኪያ የሆነው የግንባታ ወጪ በአመት ከ100% በላይ መናሩን ማመኑ፣ እንዲሁም

4ኛ/ መመሪያዎች ሲወጡ መመሪያው ለሚተገበርበት ህዝብ ግልጽ መሆን ሲኖርበት ያለመሆኑ እንዲሁም በመሬት ላይ ያሉ ነባራዊ ሁኔታዎችን ከግምት ውስጥ ያላስገባ መሆኑ

ግርምትን አጭሮብኛ

Via Tilahun Girma

@etconp