Get Mystery Box with random crypto!

በሀገረ ሶርያ ከቆሻሻና ካገለገሉ የፕላስቲክ ቁሶች የሚሰሩ ምንጣፎች በሰሜን ምዕራብ ሶርያ የሚኖ | Ethiopian Construction Work Professionals - ETCONp

በሀገረ ሶርያ ከቆሻሻና ካገለገሉ የፕላስቲክ ቁሶች የሚሰሩ ምንጣፎች

በሰሜን ምዕራብ ሶርያ የሚኖሩ ነዋሪዎች ያገለገሉ የፕላስቲክ ውጤቶችን እንደገና ጥቅም ላይ በማዋል የተለያዩ ውበት ያላቸው የወለል ምንጣፎችና ሌሎች ዕቃዎችን  ያመርታሉ።

የ39 ዓመት ዕድሜ ያለው ሞሐመድ ቢላል የሰሜን ምዕራብ ሶርያ ነዋሪ ሲሆን ከቆሻሻ መጣያ ውስጥ እንደገና ጥቅም ላይ የሚውሉ ፕላስቲኮችን በመሰብሰብ ምንጣፎችን ለሚያመርቱ ፋብሪካዎች ያስረክባል፡፡ በሳምንት ከ7 እስከ 10 የአሜሪካ ዶላር ያገኛል።

የምንጣፍ ፋብሪካው ባለቤት ካሊድ ራሹ ፤ቢላል እና መሰሎቹ የሚሰበስቡትን ቆሻሻ ፕላስቲክ ቁሳቁሶች በመግዛት በየፈርጁ በመለየት በማቅለጥ የተለያዩ ቅርጽ ያላቸውን ምንጣፎች ይሰራል፡፡

በፋብሪካው ውስጥ "ከ30 በላይ ሠራተኞች አሉን" ያለው ካሊድ ራሹ ብዙዎች ሥራ አጥ በሆኑበት በዚህ አካባቢ ስራ መፍጠር ትልቅ ቦታ አለው ብሏል።

የ30 ዓመቱ የሱቅ ባለቤት የሆነው መሐመድ አልቃሴም በካሊድ ራሹ ፋብሪካ የሚሰሩ ምንጣፎችን ከሚሸጡ ሰዎች መካከል አንዱ ነው።

ምንጣፉ ከ5 እስከ 15 የአሜሪካ ዶላር የሚያወጣ ሲሆን ባሕላዊ ምንጣፎች ደግሞ 100 የአሜሪካ ዶላር ገደማ ዋጋ እንዳላቸው መሃመድ ገልጿል።

ምንጣፎቹ ሙቀት የማይስቡ በመሆናቸው በሙቀት ወቅት ተፈላጊነታቸው እንደሚጨምር እና ዋጋቸውም ተመጣጣኝ መሆኑን  መሃመድ ለአልጀዚራ ተናግሯል።

@etconp