Get Mystery Box with random crypto!

አረንጓዴ ህንጻ ደረጃ መስፈርቶች የተያያዘው ሰሌዳ በተለያዩ አገራት ዘንድ ለአረንጓዴ ወይም ለዘላ | Ethiopian Construction Work Professionals - ETCONp

አረንጓዴ ህንጻ ደረጃ መስፈርቶች

የተያያዘው ሰሌዳ በተለያዩ አገራት ዘንድ ለአረንጓዴ ወይም ለዘላቂ ህንጻ የሚሰጠውን ደረጃ አይነት በተነጻጻሪነት ያሳያል፡፡ የአገራችንም ህንጻ ነዳፊዎች፣ ለአገራችን የሚስማማ የአረንጓዴ ህንጻ ደረጃ መስፈርት ማውጣት ይኖርባቸዋል፡፡ የአገራችን ህንጻ ነዳፊዎች በብዙ የሙያቸው ጉዳይ ላይ ግንባር ቀደም መሆንና አስቀድሞ ተራማጅ (Proactive) መሆን ያንሳቸዋል፡፡

የጎረቤት ኬንያ የህንጻ ነዳፊዎች ማህበር “Safari Green Building Index” የተባለ የአረንጓዴ ህንጻ ደረጃ መስፈርት አበጅተው ስራ ላይ አውለውታል፡፡

ሀገራችን ይህንን የራሳችንን ደረጃ ለመጀመር እና ትምህርት ለመቅሰም ያህል ህንጻ ነዳፊዎቻችን EDGE (Excellence in Design for Greater Efficiencies) የተባለውን በአለም ባንክ ስር የሚዘጋጀውንና በአሁኑ ሰአት በአለም አገራት ዘንድ ተቀባይነቱ እየጨመረ የመጣውን የአረንጓዴ ህንጻ ምስክርነት ስርአት እንዲማሩና በአረንጓዴ ህንጻ ንድፍ እና ግንባታ የተመሰከረላቸው እንዲሆኑ መጎትጎት ያሻል፡፡

ለዚህም የኢትዮጵያ አርክቴክቶች ማህበር ግንባር ቀደሙን ሚና መጫወት ይኖርበታል ይህ ካልሆነ ግን እንደሌላው ግዜ ሁሉ በሌሎች ባለሙያዎች ተፈትፍቶ የቀረበ እና ለሙያው ያልመጠነ ሰነድ ተዘጋጅቶ ለማህበሩ ሊወረወርለት እንደሚችል መገመት አይከብድም፡፡

@etconp