Get Mystery Box with random crypto!

በጠየቃቹን መሰረት መያዥያ ገንዘብ (Retention money) እና ቅደመ ክፍያ (ADVANCE | Ethiopian Construction Work Professionals - ETCONp

በጠየቃቹን መሰረት

መያዥያ ገንዘብ (Retention money) እና
ቅደመ ክፍያ (ADVANCE PAYMENT) አብራሩልን ላላቹ

ቅደመ ክፍያ (ADVANCE PAYMENT)

በልዩ ሁኔታ ለፕሮጀክቱ የተዘጋጀው የኮንትራት ውል ቅድሚያ ክፍያ/advance payment/ የሚፈቅድ ከሆነ ስራ ተቌራጩ ስራውን ለማሰጀመር ማሽነሪ እና የግንባታ ግብአት ለማስገባት በሚጠየቅ ግዜ የሚከፈል ክፍያ ሲሆን ከዚህ በታች የተጠቀሱትን ቅድመ ሁኔታዎች መሟላት ይኖርባቸዋል

ቅድመ ክፍያው ስራ ተቋራጩን የሰራ ውሉን ተፈፃሚ የሚያደርግበትን የጠቅላላ ግምት ነው።
በልዩ ሁኔታ የተዘጋጀው የኮንትራት ውል(Special condition of contract) የቅድሚያ ክፍያውን መጠን መግለፅ ሲኖርበት ነገር ግን ከጠቅላላ ፕሮጀክት ወጪ ሰላሳ (30%)ፐርሰንት መብለጥ የለበትም።
ውል ተፈፅሞ ፕሮጀክት ሳይት ርክክብ ሳይደረግ ቅድሚያ ክፍያ አይሰጠውም።
ስራ ተቋራጩ ለሚወስደው ክፍያ ዋስትና ቦንድ ሊያቀርብ ይገባል።

መያዥያ ገንዘብ (Retention money)

ስራ ተቋራጩ የተሰጠውን ስራውን ጨርሶ የስህተት ማስተካከያ ግዜ ድረስ/defect liability period / ሀላፊነት
ለመወጣቱ ማረጋገጫ እንዲሆን ከእያንዳንዱ የክፍያ ቅፅ የሚያዝ
ገንዘብ ነው።

ከክፍያ ቅፅ ምን ያህል ሊቆረጥበት እንደሚገባ ለፕሮጀክቱ በልዪ ሁኔታ የተዘጋጀው ውል/special condition of contract/በግልፅ ሊያስቀምጥ ይገባል።

ሆኖም ከ አስር ፐርሰንት (10%) የበለጠ መሆን አይችልም።

በሀገራችን አብዛኛውን ግዜ አምስት ፐርሰንት(5%) ብቻ የተለመደ ነው።

ስራው እንደተጠናቀቀ ግማሹ ከመጨረሻ ክፍያ ጋር ቀሪው ደግሞ ከርክክብ በኋላ ስራው ላይ ስህተት ቢፈጠር በውሉ ላይ የማስተካከያ ቀነ ገደብ ሲጠናቀቅ ከመጨረሻ ርክክብ ጋር በአርባ አምስት (45) ቀናት ውስጥ ይለቀቅለታል።

@etconp