Get Mystery Box with random crypto!

☞በኮንስትራክሽን ስራ ውጤታማ ለመሆን የሚያስፈልጉ COTM/ ሲቪል ኢንጅነር ሊያውቃቸው የሚገቡ 10 | Ethiopian Construction Work Professionals - ETCONp

☞በኮንስትራክሽን ስራ ውጤታማ ለመሆን የሚያስፈልጉ COTM/
ሲቪል ኢንጅነር ሊያውቃቸው የሚገቡ 10 ወሳኝ ነጥቦች...
.
1) የግንባታ እቃዎች ፍተሻ( TESTS OF BUILDING
MATERIALS) አንድ ጥሩ ኢንጅነር በሳይት ላይ የሚሰሩ
የግንባታ እቃዎችን ለመፈተሽ
የሚጠቅሙ የፍተሻ ስራዎችን የግድ ማወቅ ይጠበቅበታል።
ከታች የተለያዩ
አይነት የፍተሻ ቴክኒኮች ተጠቅሰዋል
የኮንክሪት ፍተሻ(Concrete Test):
•Slump test,
•compression test (cubic or cylindrical test),
•split tensile test, soundness etc.
የአፈር ፍተሻ (Soil Test):
•Core cutter test,
•compactiontest,sand replacement test, triaxial test,
consolidation test etc.
Bitumen Test:
•Ductility test, softening point
test, gravity test, penetration test etc.
(በእርግጥ እነዚህን ሁሉ እውቀቶች በየዮንቨርስቲዎች ውስጥ
አንማር ይሆናል
ነገር ግን ዘመኑ የቴክኖሎጂ ነው ተወዳዳሪ ሆኖ ለመቅረብ የግድ
መማር
ማወቅ አለብን ዩ ቲዩብ ገብተን ብንፈልግ በቪድዮ የተደገፉቁም
ነገሮችን እናገኛለን ጥቆማችን ነው ::
:
2) የአፈር ጥናት (INVESTIGATION OF SOIL)
የተለያዩ አይነት የፍተሻ ቴክኒኮችን ተጠቅመን የአፈሩን የመሸከም
አቅም እና
ርጉእነት (settlement and stability ) የምንገነባው አካል
ከመገንባቱ በፊት ልናውቅ እንችላለን።
እንደ ኢንጅነር የአፈር ጥናት ለማድረግ የሚጠቅሙ
በሳይት ላይ የሚከወኑ የፍተሻ ቴክኒኮችን ማወቅ ግዴታችን ነው።
:
3 የተለያዩ የሰርቬይን መሳሪያዎች አጠቃቀም ማወቅ(USES OF
SURVEYING INSTRUMENTS)
በእርግጥ በብዙ የኮንስትራክሽን ስራዎች ላይ ራሱን የቻለ
የሰርቬይ ባለሞያ መቅጠር አሁን አሁን የተለመደ ቢሆንም ነገር
ግን መሰረታዊ የሚባሉ የሰርቬይ
መሳራያዎች ለምሳሌ ቶታል ስቴሽን እና ቴዎዶላይት
አጠቃቀማቸውን አንድ ኢንጅነር የግድ ማወቅ አለበት። የግድ !
:
4). የተለያዩ የግንባታ ስታንዳርድ ኮዶች (STANDARD CODES
USED IN CONSTRUCTION)
ኢትዮጵያን ጨምሮ የተለያዩ ሃገራት ከመልካ ምድራቸው
የአየር፣የንፋስ፣የመሬት መንቀጥቀጥ ከባቢያዊ ፀባያቸው አንፃር
የሚያዘጋጁት የግንባታ መርህ
(Construction codes) አላቸው።
አንድ ኢንጅንየር ግንባታ የሚያደርግበት ሃገርን ስታንዳርድ ኮድ
የማወቅ ግዴታ አለበት ምክንያቱም የሚገነባው ቁስሃገሪቱ ባላት
ተፈጥሯዊ መሰናክል እንዳይሰናከል እና እንዳይወድም። እነዚህን
ኮዶች ወይም መመሪያዎች ሳይከተል የሚገነባ የትኛውም ግንባታ
የመፍረስአቅሙ በእጥፍ የጨመረ ነው።

5) BAR BENDING SCHEDULE
ባር ቤንዲንግ ስኬጁል ለኢንጅነየሮች ጠቃሚ የሆነ ቻርት (በተለይ
ኮንስትራክሽኑ ሬንፎርስመንት ካለው)። ይህ ቻርት ሬንፎርስድ
የሆነው የግንባታ
አካል ማለትም ቢም፣ኮለን፣ስላብ፣ዋል...የሚጠቀማቸውን ቤረቶች
የሚቆረጥበት ርዝመት ፣ በምን ያህል ርዝመት እንደሚታጠፉ እና
ምን ያክል ተመሳሳይ እጥፋትና ርዝመት ያላቸው ባሮች በዛ አካል
ውስጥ እንደሚኖሩ በግልፅ ይነግረናል ።
ይህ ቻርት ብረትን ያለብክነት እንድንጠቀም እና የስትራክቸሩን
ደህንነት (safety) እንድንጠብቅ ይጠቅመናል

6) የንድፍ እና ዲዛይን ንባብ (DRAWING AND DESIGN)
አንድ ሳይት ኢንጅነር ከምንም ከምንም በላይ የግንባታን ንድፍ
የማንበብ በጣም ትልቅ እውቀት ሊኖረው ይገባል።
ዲዛይን እና ንድፎችን በትክክል ማንበብ እናመተርጎም ከቻለ
ለሳይት ኢንጂንየርነት የሚያበቃውን 60% እውቀት አካብቷል
ማለት ነው።
ስለዚህ በተለይ ተማሪዎች ለቴክኒካል ድራዊንግ እና አውቶካድ
እውቀቶች የምትሰጡትን ክሬዲት ከፍ አርጉ የፔጃችን መልእክት
ነው::

7) ግምት እና ክፍያ ( ESTIMATION AND BILLS)
ግንባታው ምን ያህል ገንዘብ እንደሚያወጣ ግምቱን
የሚያስቀምጠው የሳይት ኢንጅንየሩ ነው።
(እንዴት መገመት እንዳለብን ፎርማቱን ወደፊት እንፖስታለን)

8 የጥራት ቁጥጥር (QUALITY CONTROL)
ከኢንጅነሪንግ መርሆች ውስጥ አንዱ ጥራት ነው።
ጥራቱን የጠበቀ ግንባታ
ለተጠቃሚው አካል ገንብቶ ማቅረብ ግዴታችን ነው።
አንዳንዴ ለሆዳቸው ያደሩኢንጂንየሮች ጥራቱን ባልጠበቀ የግንባታ
መሳሪያ ገንብተው ያስረከቡት ህንፃ ምን አይነት ጉዳቶች እንዳደረሰ
የቅርብ ግዜ ትዝታችን ነው።
አንድ ሳይት ኢንጅነር የሚጠቀመውን የግንባታ ቁስ ጥራት
የማወቅ ግዴታ አለበት ኋላ በሃገርም በግለሰብም ላይ የሚደርስን
አደጋ ለመከላከል።

9) የሳይት ላይ አመራሮች (ON FIELD MANAGEMENT)
እንዴት ፎርም ወርክ መታሰር እንዳለበት፣ የኮንክሪት አሰራር፣
ለጥንቃቄ
የምንሰራቸው ስራዎችን ጨምሮ የተለያዩ ነገሮች ማወቅ ግዴታችን
ነው
:
10) ከጉልበት ሰራተኞች ጋር ያለን መናበብ መቀራረብ
(COORDINATION
WITHLABOR) የጉልበት ሰራተኞችን ጨምሮ ሌሎች የተማሩ
እና ያልተማሩ ሰራተኞችን እንዴትማስተዳደር እንዳለብን እውቀቱ
ሊኖረን ይገባል።
ትዛዝ ማስተላለፍ ብቻሳይሆን ወርዶ መስራትም ይጠበቅብናል።
ለስራችን መቀላጠፍ ከሁሉምጋ ተናቦና በፍቅር መስራት ወሳኝ እና
ወሳኝ ነገር ነው።
.
.
አንድ ጥሩ የሚባል CONSTRUCTION እንጅነር ማወቅ ስለሚገባው ነገሮች ትንሽም ቢሆን እውቀት እንደሰጠናቹ ተስፋ አረጋለው።

@etconp

Facebook:- https://www.facebook.com/etconp/