Get Mystery Box with random crypto!

የቁቤ ትውልድ ይለያል ስልህ በምክንያት ነው Yahya Mohammed Abdela ይባላል፡፡ ትውል | ESSA YUSUF

የቁቤ ትውልድ ይለያል ስልህ በምክንያት ነው

Yahya Mohammed Abdela ይባላል፡፡ ትውልድ እና እድገቱ የምስራቅ ሀረርጌ መቀመጫ በሆነችው የበረሃዋ ንግስት ድሬዳዋ ነው፡፡ በቴክኖሎጂው በተለይም በሳይበር ሴኩሪቲ እና ሶፍትዌር ኢንጂነሪንግ ወደፊት ኦሮሚያ ተስፋ ከጣለችባቸው የቁቤ ትውልድ መሃል አንዱ ነው፡፡

በአሁኑ ሰአትም በsothern california university ውስጥ በcyber security ትምህርቱን እየተከታተለ ይገኛል፡፡ ከgulf online class አፕሊኬሽን የማበልጸግ ሰርተፍኬት ተቀብሏል፡፡ በአጠቃላይ ከ20 በላይ APP በ playstore ላይ ሰርቶ አስቀምጧል፡፡

ያህያ ከዚም በተጨማሪ ፀሃፊ ነው፡፡ ROLE OF HARARGE IN ETHIOPIA (የሃረርጌ ሚና በኢትዮጵያ ውስጥ) የሚል መፅሃፍ አሳትሞ በኦንላይን እየሸጠ ይገኛል፡፡

ከሰሞኑ ደግሞ በምስራቅ አፍሪካ የዌብሳይት አበልፃጊዎች ግሩፕ ባዘጋጁት ውድድር ላይ ተሳትፎ ሁለተኛ በመውጣት አጠናቋል፡፡ በዚህም መሰረት ይህንን ግሩፕ ለመቀላቀል ችሏል፡፡ ይህ ግሩፕ በዋነኝነት የሚሰራው በምስራቅ አፍሪካ IGAD ውስጥ ከዌብሳይት ጋር የተያያዙ ጉዳዮች ላይ ያጠነጥናል እናም ያህያ ከሰሞኑ በonline በተደረገ ድምፅ አሰጣጥ መላው የኦሮሞ ህዝብ በሰጠው ድምፅ ምክንያት ከአፍሪካ ከተውጣጡ ወጣቶች ጋር ተወዳድሮ በማሸነፍ ይህን ግሩፕ ሊቀላቀል ችሏል፡፡

ታድያ ይሄ ቁቤ ትውልድ በተለያዩ ዘርፎች ላይ በአለም ላይ ተፀዕኖ መፍጠሩን ተያይዞታል፡፡ የኦሮሞ ህዝብም ልጆቹን ሊያበረታታ እና ከጎን ቆሞ ሊደግፍ ይገባል፡፡

ኦቦ ያህያ ያገኘሃው እድል በጣም ትልቅ ነው ታላቅ የሆነውን ህዝብ ወክለህ ነው ያለሀው በርትተህ ትልቅ ቦታ እንደምትደርስ ተስፋ አለኝ፡፡ ባገኘሃው እድል በጣም ኮሪቼብሃለው በርታልን፡፡ ያለህን እውቀት እና ችሎታ ለቀጣዩ ትውልድ መንገድ ሆነህ እንደ አርአያ እንደምትሆን አልጠራጠርም፡፡

እኛ የቁቤ ትውልዶች ውድድራችን ከአለም ጋር ነው