Get Mystery Box with random crypto!

ኢትዮጲያ በየአመቱ የምታከብረው አዲስ አመት (ዘመን መለወጫ) (እንቁጣጣሸ) እኛ ሙስሊሞችን አይመለ | 📖//እስላሚክ⚡️⚡️TŰB€//📖

ኢትዮጲያ በየአመቱ የምታከብረው አዲስ አመት (ዘመን መለወጫ) (እንቁጣጣሸ) እኛ ሙስሊሞችን አይመለከትም!
ስለምን ካሉ ምክንያታችንን በትዕግስት ያንብቡ! ሀገራት እራሳቸውን የቻለ የጊዜ ሰሌዳ አላቸው። ለምሳሌ ያህል አውሮፓዊያን፣
ሀገራችን ኢትዩጲያ እንዲሁም ሙስሊሞችና ሙስሊም ሀገራት የሚጠቀሙት ማለት ነው።ሀገራችን የምታከብረው አዲሱ አመት እኛ
የሀገሯ ሙስሊሞች የማይመለከተን ዋነኛው ጉዳይ አከባበሩ የክርስትና እምነት ላይ ያንጠለጠለ ነው።
• በመጀመርያ ደረጃ ከስሙ እንኳን ስንነሳ "አመተ ምህረት" ማለት ነብዩ ኢሳ(የአላህ ሰላም በእሳቸው ላይ ይሁንና) ከተወለዱ
ቡኃላ ምህረት ተደርጎልናል ብለው ስለሚያስቡ ስያሜውን አመተ ምህረት ብለው ሰይመውታል። እኛ ሙስሊሞች ደግሞ
ይህንን ግጥም አድርገን እንቃወማለን። ምክንያቱም ደግሞ ጌታችንና አምላካችን አላህ ምህረቱ ከዛሬ 2010 አመተ ልደት
የጀመረ ሳይሆን፤ የሰው ዘር ከተፈጠረ ጀምሮ ምህረቱ አለ። ወደ ፊትም ይኖራል።
• በሁለተኛ ደረጃ የዘመኑ አጠራር ከዘመነ ዩሀንስ ወደ ዘመነ ማትዩስ እያለ የተለያዩ በመፀሀፍ ቅዱስ የተጠቀሱትን ስያሜዎችን
ይጠቀማሉ።
• በሶስተኛ ደረጃ እኛ ሙስሊሞች በአሉ የማይመለከተን ጉዳይ እምነታችን ስለማንኛውም ጉዳይ ምን ማድረግ እንዳለብን
የሚያብራራልን መፀሀፍ አለን። ይህም ቁርአንና ሀዲስ ናቸው። ከዚህ ውጭ ባህል ምናምን እያልን እምነታችንን የማያዘን ነገር
አንፈፅም። በተለይ ደግሞ ከእምነታችን ተቃራኒ የሆኑ እምነቶች የሚያከብሩትን በአል ማክበርም ይሁን የደስታ መግለጫ
ማቅረብ በጥብቅ የተከለከለ ነው። ነገር ግን በሀዘናቸው ወቅት ማስተዛዘን፣ ሲታመሙ መጠየቅ፣ እርዳታ ሲያስፈልጋቸው
መርዳት፣ ሰላምታን ማቅረብ፣ በማህበራዊ(ሰርግ፣ ምርቃትና የመሳሰሉት) የደስታ ጊዚያቸው ላይ እንኳን ደስ አላቹ ማለትም
ይሁን መሳተፍ አልተከለከልንም።
ስለዚህ የተከበራቹ ሙስሊም ወንድሞቼ! ከሀዲያን ቅር እንዳይላቸው፣ ግንኙነታችን እንዳይሻክር፣ ባህል ምናምን እያልን
እምነታችንን የሚቃረን ነገር ከመፍጠር እንታቀብ።
አንዳንድ ሰው ብዙ አመት ሳደርገው የነበርኩት ነገር ነው እንዴት ላቁመው ብለው ይጨናነቃሉ ወላሂ ከልብ ከነየቱ(ካሰቡ)
ይቻላል።
• " ሰዎች ይደሰቱ አላህ ይቀየም የሚሉ፤ ታላቁ ጌታችን አላህም ጠልቷቸው እነዛ እንዳይቀየሙ ብሎ የሳሱላቸው እንዲጠሉትያደርጋል ብለዋል ረሱላችን ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም!በተቃራኒው አላህ ይደሰት ሰዎች ቅር ይበላቸው ብሎ የጌታቸውን ትእዛዝ ያከበሩትን አላህ ወዷቸውም
ሰዎችም እንዲወዷቸው ያደርጋል።" ወወላሂ፣ ወቢላሂ፣ ወተላሂ ኩራት አደለም በስራም ቦታ ይሁን ጎረቤት ይወዱኛል፣
ያከብሩኛል። ሰዎች የሚያከብሩህና የሚወዱህ የጌታህን ትእዛዝ ችላ ስላልክ አደለም። ለዚህም ነው አንድ ወንድማችን ፂሙ
ረዥም ነበርና ስራ ለመቀጠር ብዙ ተቸገረ። እናም የስራ ማጣቱ ምክንያት የፂሙ መርዝም ነው ብሎ እርግፍ አደረገውና ከዚህ
በፊት ጠይቋቸው ከነበሩት ውስጥ በድጋሚ ወደ አንዱ መስሪያ ቤት ሲሄድ አንተ የጌታህን ትእዛዝ ለስራ ብለህ ከተውክ
ለድርጅታችን እንዴት ታማኝ ልትሆን ትችላለህ ብለው ደና ሰንብት አሉት። የገባው ይገበዋል። ጌታውን አስከፍቶ ፍጡር
ማስደሰት ከሁለቱም ያጣ ይሆናል፤ በተቃራኒው ጌታው ያስደሰተ ፉጡሮች ይወዱታል እንጂ አይጠሉትም! ቢጠሉትም የአላህ
ወዳጅ ጠላኝ ብሎ ለሰከንድም ማሰብ አግባብ አደለም!