Get Mystery Box with random crypto!

'ተወኩል ' አብዛኛው ሰው በአላህ መመካት ማላት ምን ማለት እንደሆነ ግክፅ ግንዛቤ የላቸውም | 📖//እስላሚክ⚡️⚡️TŰB€//📖

"ተወኩል "


አብዛኛው ሰው በአላህ መመካት ማላት ምን ማለት እንደሆነ ግክፅ ግንዛቤ የላቸውም:: ከፊሎች ምክንያት(ሰበቡን ) በማድረስ፣ ሀላፊነትን በመወጣት ብቻ ይብቃቀሉ ::እነዝህ ረዥሙን መንገድ ብቻቸውን ለመጏዝ ይገደዳሉ ::ሌሎች ደግሞ እጃቸውን አጣጥፈው ይቀመጡና የአላህን እርዳታ ይጠብቃሉ ::ሳያርሱ አዝመራን ፣ሳይጋግሩ መብላትን ፣ሳይታጠቡ መፅዳትን .....ይፈልጋሉ :: እነኚህ አጉል ተስፈኞች ናቸው::
እርግጥ ነው ለአላህ የሚሳነው የለም ::ያለእኛ ተሳትፎ የምንፈልገውን ነገር ሁሉ ሊያሟላልን ይችላል ::ነገር ግን የምድርን ስርኣት እንዲህ አይደለም ያስቀመጠው ::የኣደም ልጆች በሁለት ክንፍ እንዲበሩ ይፈልጋል ::አንደኛው ክንፍ በእርሱ ላይ መመካት ሲሆን ፣ሌላኛው ሰበቦችን ማድረስ ::የስኬት ምንጩ በአላህ መደገፍ ነው :: የስኬትን ረዥም ጉዞ ብቻህን አትችላውም ::በራስ ተብቃቅቶ መጏዝ ወንዝ አያሻግርም ::በግል ጥረት ዳር ለመድረስ የሚጥር ሁሉ ለግል ጥረታቸው ይታዋሉ :: ትልቁን ከፍታ ብቻቸውን ለመውጣት ይገደዳሉ :: ያ በአላህ የተመካው ግን በስንዝር ጥረት የክንድ ያህል ያራመዳል::ከጥረቱ በላይ ውጤት ያገኛል :: አስታውስ የተኛ ውሃ ይሸታል፤ የታሰረ ወፍ ይሞታል፤ የተጠፈነገ አንበሣ ይዋረዳል ። የሰው ልጅ በአንድ ቦታ ላይ ሆኖ ውጤት ማምጣት አይቻለውምና በአንድ ቦታ አትቀመጥ
አደራህን አትሰልች አትታክት፣ ስልቹ ሰው ግዴታውን የመወጣት ብቃት የለውም፡፡ የሚታክት ሰው ክብሩን አይጠብቅም፡፡ ስለሆነም ታገስ፤ በርታ ፤ ጽና፡፡