Get Mystery Box with random crypto!

ቆም ብለህ አስተንትን አትዘን ፦ ቀድሞ በታዘዘና ባትፈልገውም በተወሰነና በማይቀር | 📖//እስላሚክ⚡️⚡️TŰB€//📖

ቆም ብለህ አስተንትን

አትዘን

ቀድሞ በታዘዘና ባትፈልገውም በተወሰነና በማይቀር ነገር ላይ አትዘን ። እያንዳንዱ ጉዳይ በፅኑ ተወስኗል ። ቀለሞች ደርቀዋል ። ወረቀቶቹ ተከድነዋል ። ሥለዚህ ማዘንህ እውነታውን በትንሹም ቢሆን አይቀይረውም ።
አትዘን

ምክንያቱም ከማዘንህ ጋር ጊዜ እንዳይፈራረቅ ፣ ፀሀይ ባለችበት እንድትቀር ፣ እጅህ ላይ ያለው ሰዓት እንድቆም ፣ እርምጃህ ወደኋላ እንድሆን ፣ ወንዙ ወደ መነሻው እንድፈስ ትፈልጋለህ ።
አትዘን

ሀዘን ሞገደኞችን በአደገኛ ሁኔታ የሚወረውር ፣ ከባቢ አየርን የሚቀይር ፣ በማራኪ አትክልት ቦታ ላይ ያሉ ውብ አበቦችን የሚያወድም አውሎ ንፋስ ነው ።
አትዘን

ሀዘን ላይ ያለ ሰው ቀዳዳ ባሊ ውስጥ ያለ ውሀ እንደሚያንቆረቁርና በጣቱ ውሀ ላይ ፅሁፍ ለመፃፍ እንደሚሞክር ነው ።
አትዘን

የህይወት ትክክለኛ ዋጋ የሚለካው በሰላም ባሳለፍካቸው ቀናት ብቻ ነው ። ጊዜህን በመከራ በማሳለፍ አታባክን ። አሏህ አባካኞችንና አክሳሪወችን አይወድም ።
አትዘን

በእርግጥም ጌታህ ሀጢዓትን ይምራል ፤ ተውበትን ይቀበላል ። ቀጣዩን አንቀፅ ስታነብ ልብህ ሰላም አያገኝም ? ጭንቀትህ አይወገድም ? ደስታ በሰራ አካልህ አይሰራጭም ?
۞ ﻗُﻞْ ﻳَﺎ ﻋِﺒَﺎﺩِﻱَ اﻟَّﺬِﻳﻦَ ﺃَﺳْﺮَﻓُﻮا ﻋَﻠَﻰٰ ﺃَﻧﻔُﺴِﻬِﻢْ ﻻَ ﺗَﻘْﻨَﻄُﻮا ﻣِﻦ ﺭَّﺣْﻤَﺔِ اﻟﻠَّﻪِ ۚ ﺇِﻥَّ اﻟﻠَّﻪَ ﻳَﻐْﻔِﺮُ اﻟﺬُّﻧُﻮﺏَ ﺟَﻤِﻴﻌًﺎ ۚ ﺇِﻧَّﻪُ ﻫُﻮَ اﻟْﻐَﻔُﻮﺭُ اﻟﺮَّﺣِﻴﻢُ
በላቸው «እናንተ በነፍሶቻችሁ ላይ ድንበር ያለፋችሁ ባሮቼ ሆይ! ከአላህ እዝነት ተስፋ አትቁረጡ፡፡ አላህ ኃጢኣቶችን በመላ ይምራልና፡፡ እነሆ እርሱ መሓሪው አዛኙ ነውና፡፡
(አል-ዙመር )
ባሮቼ ሆይ ! ሲል ጠራቸው ወደሱ ቀረብ በማድረግ ። በጥመት ላይ ያሉ ሰወች ከሌሎቹ ይልቅ በተደጋጋሚ መጥፎ ተግባራትን ለመፈፀም የተጋለጡ ስለሆኑ ነው በተለይ የጠቀሳቸው ። የአሏህ እዝነት ምን ያህል ታላቅ ነው ?? ስለዚህም ምህረት ከማግኜት ተስፋ እንዳይቆርጡ አበረታታቸው ። ሀጥያቱ ትልቅም ይሁን ትንሽ ፣ ጠቃሚም ይሁን ጠቃሚ ያልሆነ የተፀፀተን ሰው እንደሚምር አሳወቃቸው ።
ቀጣዮቹን አንቀፆች ስታነቡ በደስታ አትፈነጥዙም ??
ﻭَاﻟَّﺬِﻳﻦَ ﺇِﺫَا ﻓَﻌَﻠُﻮا ﻓَﺎﺣِﺸَﺔً ﺃَﻭْ ﻇَﻠَﻤُﻮا ﺃَﻧﻔُﺴَﻬُﻢْ ﺫَﻛَﺮُﻭا اﻟﻠَّﻪَ ﻓَﺎﺳْﺘَﻐْﻔَﺮُﻭا ﻟِﺬُﻧُﻮﺑِﻬِﻢْ ﻭَﻣَﻦ ﻳَﻐْﻔِﺮُ اﻟﺬُّﻧُﻮﺏَ ﺇِﻻَّ اﻟﻠَّﻪُ ﻭَﻟَﻢْ ﻳُﺼِﺮُّﻭا ﻋَﻠَﻰٰ ﻣَﺎ ﻓَﻌَﻠُﻮا ﻭَﻫُﻢْ ﻳَﻌْﻠَﻤُﻮﻥَ
ለእነዚያም መጥፎ ሥራን በሠሩ ወይም ነፍሶቻቸውን በበደሉ ጊዜ አላህን የሚያስታውሱና ለኀጢአቶቻቸው ምሕረትን የሚለምኑ ለኾኑት ከአላህም ሌላ ኀጢአቶችን የሚምር አንድም የለ፡፡ (በስሕተት) በሠሩትም ላይ እነርሱ የሚያውቁ ሲኾኑ የማይዘወትሩ ለኾኑት (ተደግሳለች)፡፡)
(አል-ዒምራን
ﻭَﻣَﻦ ﻳَﻌْﻤَﻞْ ﺳُﻮءًا ﺃَﻭْ ﻳَﻈْﻠِﻢْ ﻧَﻔْﺴَﻪُ ﺛُﻢَّ ﻳَﺴْﺘَﻐْﻔِﺮِ اﻟﻠَّﻪَ ﻳَﺠِﺪِ اﻟﻠَّﻪَ ﻏَﻔُﻮﺭًا ﺭَّﺣِﻴﻤًﺎ
መጥፎም የሚሠራ ሰው ወይም ነፍሱን የሚበድል ከዚያም (ተጸጽቶ) አላህን ምሕረት የሚለምን አላህን መሓሪ አዛኝ ኾኖ ያገኘዋል፡፡
(አል-ኒሳዕ )
ﺇِﻥ ﺗَﺠْﺘَﻨِﺒُﻮا ﻛَﺒَﺎﺋِﺮَ ﻣَﺎ ﺗُﻨْﻬَﻮْﻥَ ﻋَﻨْﻪُ ﻧُﻜَﻔِّﺮْ ﻋَﻨﻜُﻢْ ﺳَﻴِّﺌَﺎﺗِﻜُﻢْ ﻭَﻧُﺪْﺧِﻠْﻜُﻢ ﻣُّﺪْﺧَﻼً ﻛَﺮِﻳﻤًﺎ
ከእርሱ ከተከለከላችሁት ታላላቆቹን (ኀጢአቶች) ብትርቁ (ትናንሾቹን) ኀጢአቶቻችሁን ከእናንተ እናብሳለን፡፡ የተከበረንም ስፍራ (ገነትን) እናገባችኋለን፡፡
(አል-ኒሳዕ )
ﻭَﻣَﺎ ﺃَﺭْﺳَﻠْﻨَﺎ ﻣِﻦ ﺭَّﺳُﻮﻝٍ ﺇِﻻَّ ﻟِﻴُﻄَﺎﻉَ ﺑِﺈِﺫْﻥِ اﻟﻠَّﻪِ ۚ ﻭَﻟَﻮْ ﺃَﻧَّﻬُﻢْ ﺇِﺫ ﻇَّﻠَﻤُﻮا ﺃَﻧﻔُﺴَﻬُﻢْ ﺟَﺎءُﻭﻙَ ﻓَﺎﺳْﺘَﻐْﻔَﺮُﻭا اﻟﻠَّﻪَ ﻭَاﺳْﺘَﻐْﻔَﺮَ ﻟَﻬُﻢُ اﻟﺮَّﺳُﻮﻝُ ﻟَﻮَﺟَﺪُﻭا اﻟﻠَّﻪَ ﺗَﻮَّاﺑًﺎ ﺭَّﺣِﻴﻤًﺎ
ማንንም መልክተኛ በአላህ ፈቃድ ሊታዘዙት እንጅ አልላክንም፡፡ እነሱም ነፍሶቻቸውን በበደሉ ጊዜ ወደ አንተ ቢመጡና አላህንም ምሕረትን በለመኑ መልክተኛውም ለነርሱ ምሕረትን በለመነላቸው ኖሮ አላህን ጸጸትን ተቀባይ አዛኝ ኾኖ ባገኙት ነበር፡፡
(አል-ኒሳዕ )
ﻭَﺇِﻧِّﻲ ﻟَﻐَﻔَّﺎﺭٌ ﻟِّﻤَﻦ ﺗَﺎﺏَ ﻭَﺁﻣَﻦَ ﻭَﻋَﻤِﻞَ ﺻَﺎﻟِﺤًﺎ ﺛُﻢَّ اﻫْﺘَﺪَﻯٰ
እኔም ለተጸጸተ፣ ላመነም፣ መልካምንም ለሠራ፣ ከዚያም ለተመራ ሰው በእርግጥ መሓሪ ነኝ፡፡
(ጣሃ )
ነብዩሏህ ሙሳ አለይሂ ሰላም አንድን ሰው በገደሉ ጊዜ *ጌታዬ ሆይ ማረኝ * በማለት ለመኑ ። አሏህም ማራቸው ። ነብዩሏህ ዳውድ አለይሂ ሠላም ተውበት ባደረጉ ጊዜ አሏህ የሚከተለውን ብሏቸዋል ።
ﻓَﻐَﻔَﺮْﻧَﺎ ﻟَﻪُ ﺫَٰﻟِﻚَ ۖ ﻭَﺇِﻥَّ ﻟَﻪُ ﻋِﻨﺪَﻧَﺎ ﻟَﺰُﻟْﻔَﻰٰ ﻭَﺣُﺴْﻦَ ﻣَﺂﺏٍ
ለእርሱም እኛ ዘንድ መቅረብ (ክብር) መልካም መመለሻም አለው፡፡
(ሷድ )
አሏህ ምንኛ የጠራ ፤ አዛኝና ለጋስ ጌታ ነው ። በሶስቱ ስላሴ ለሚያምኑት ሳይቀር ከተፀፀቱ እዝነቱንና ምህረቱን አቅርቦላቸዋል ።
ﻟَّﻘَﺪْ ﻛَﻔَﺮَ اﻟَّﺬِﻳﻦَ ﻗَﺎﻟُﻮا ﺇِﻥَّ اﻟﻠَّﻪَ ﺛَﺎﻟِﺚُ ﺛَﻼَﺛَﺔٍ ۘ ﻭَﻣَﺎ ﻣِﻦْ ﺇِﻟَٰﻪٍ ﺇِﻻَّ ﺇِﻟَٰﻪٌ ﻭَاﺣِﺪٌ ۚ ﻭَﺇِﻥ ﻟَّﻢْ ﻳَﻨﺘَﻬُﻮا ﻋَﻤَّﺎ ﻳَﻘُﻮﻟُﻮﻥَ ﻟَﻴَﻤَﺴَّﻦَّ اﻟَّﺬِﻳﻦَ ﻛَﻔَﺮُﻭا ﻣِﻨْﻬُﻢْ ﻋَﺬَاﺏٌ ﺃَﻟِﻴﻢٌ
እነዚያ «አላህ የሦስት ሦስተኛ ነው» ያሉ በእርግጥ ካዱ፡፡ ከአምላክም አንድ አምላክ እንጅ ሌላ የለም፡፡ ከሚሉትም ነገር ባይከለከሉ ከነሱ እነዚያን የካዱትን አሳማሚ ቅጣት በእርግጥ ይነካቸዋል፡፡
ﺃَﻓَﻼَ ﻳَﺘُﻮﺑُﻮﻥَ ﺇِﻟَﻰ اﻟﻠَّﻪِ ﻭَﻳَﺴْﺘَﻐْﻔِﺮُﻭﻧَﻪُ ۚ ﻭَاﻟﻠَّﻪُ ﻏَﻔُﻮﺭٌ ﺭَّﺣِﻴﻢٌ
ወደ አላህ አይመለሱምና ምሕረትን አይለምኑትምን አላህም መሓሪ አዛኝ ነው፡፡
(አል-ማዒዳህ )
ነብዩ ሶለሏሁ አለይሂ ወሠላም በሶሂህ ሀድሳቸው አሏህ ሱብሀነሁ ወተዓላ *የአደም ልጅ ሆይ ! እኔን አትለምነኝም ፤ ከእኔም ተስፋ አታደርግም ፤ የምምርህ ቢሆን እንጅ ። የለመንከኝን ያህል እምርሀለሁ ። አልቀየምህም ። የአደም ልጅ ሆይ ! ሀጢዓቶችህ የሰማያትን ያህል ቁመት ቢኖራቸው ምህረትን ከጠየቅከኝ ይቅር እልሀለሁ ። አልቀየምህም ። /በመጠናቸው / ምድርን የሚሞሉ ሀጢዓቶች ይዛችሁ ብትመጡ ከእኔ ጋር ማንንም እስካላጋራችሁ ድረስ እኔም በምህረቴ የዚያኑ ያህል ወደ እናንተ እመጣለሁ * ይላል ።
ቡኻሪ እንደዘገቡት ነብዩ ሶለሏሁ አለይሂ ወሠላም የሚከተለውን ብለዋል ። አሏህ በቀን የተሰራን ሀጥያት ለመማር በማታ የምህረት እጁን ይዘረጋል ፤ በማታ የተሰራን ሀጥያት ለመማር በቀን የምህረት እጁን ይዘረጋል ። ፀሀይ በምዕራብ እስከምትወጣ ድረስ ።
በሌላ ዘገባ ባሮቼ ሆይ ! ቀንም ማታም ሀጥያት ብትሰሩ ሀጥያቶችን ሁሉ እምራለሁ ። ስለዚህ ከእኔ ምህረትን ጠይቁ ።**