Get Mystery Box with random crypto!

፡፡፡፡፡፡፡፡፡መንታ መንገድ፡፡፡፡፡፡፡፡፡ ክፍል 25 ፀሀፊ fuad seid አይደለም ባንተ | 📖//እስላሚክ⚡️⚡️TŰB€//📖

፡፡፡፡፡፡፡፡፡መንታ መንገድ፡፡፡፡፡፡፡፡፡

ክፍል 25

ፀሀፊ fuad seid

አይደለም ባንተ በኩል፡፡ አክስቶችህ ሰፈር አለኝ! ሁለታችንም አይን ለአይን ተያይተን ሳቅንና እኩል "ኢማን"
አልን። ኢማን ሁሌም እኛ ቤት መጥታ እሱ ካለ እኔን ደክሞሀል
ምናምን ብሎ ሰበብ ሰጥቶ እሱ ነበር ወደ ቤቷ የሚያደርሳት።
"እና አዉርታችኋላ!" አልኩት።
"ሁሉም አልቋል። ኒካህ ብቻ!" አለኝ እየሳቀ። ኢማን በጣም
የምወዳት የአክስቴ ልጅ ናት። በፀባዩ የምተማመንበትን ጓደኛዬን
ስለምታገባ ደስ አለኝ። የሱን ጉዳይ አዉርተን እንደጨረስን የእኔን
ጉዳይ በሙሉ ነገርኩት። ሰዒድ ለኔ በጣም አዘነና "አክረሜ ይሄ
ነገር ድግምት ሊሆን ይችላል። ብዙ ሴቶች ይወዱህ ስለነበር
አስነክተዉህ ይሆናል።" አለኝ። ወደዱኝ ከተባሉት ሴቶች
የቀረብኳቸዉ ሀያትንእናራሄልን ነዉ። ሁለቱም ደግሞ እኔን
የሚጎዳ ነገር እንደማያደርጉ እርግጠኛ ነኝ። ቢሆንም ነገሮችን
ማረጋገጡ ሳይሻል አይቀርም በሚለዉ በቁርዓን ህክምና
ጤናዬን ልንፈትሸዉ ወሰንን።
.
በነጋታዉ ለማንም ሳንናገር እኔናሰዒዶ ወደ አንድ የቁርዓን
ህክምና ማዕከል ሄድን። ብዙ ሰዉ ከኔዉ ጋር በተያያዘ ጉዳይ
ማለትም በድግምት እና በአጋንንት ተበጥብጦ ህክምና
ለማግኘት ተቀምጧል። በመሀል ከተማችን ዉስጥ እንደዚህ
ድግምት አሳሳቢ ጉዳይ መሆኑ አሳዘነኝ። ተራዬ ሲደርስ ወደ
ህክምና ክፍሉ ገባሁ። ሰዒድም አብሮኝ ገባ። አንድ ነጭ ጀለቢያ
የለበሰ ኡስታዝ ተሽከርካሪ ወንበር ላይ ተቀምጦ ችግሬን
ካዳመጠኝ በኋላ ወደ ቀጣዩ ክፍል አስገባኝ። ቀጣዩ ክፍል ሙሉ
ለሙሉ ምንጣፍ የተነጠፈበት ክፍል ነበር። የመኪናዬን ቁልፍ
እንዲሁም ሌሎች ተያያዥ የያዝኳቸዉን ነገሮች ለሰዒድ
ከሰጠሁት በኋላ ሰዉየዉ ጮክ ብሎ ቁርዓን መቅራት ጀመረ።
መጀመሪያ ድምፁ በጣም ያምር ነበር። ከዛም የሆነ ብስጭት
ዉርር አደረገኝናድምፁ አስጠላኝ። ከዚህ በኋላ ምን
እንደተፈጠረ ነቅቼ ሰዒድ እስኪነግረኝ ድረስ አላዉቅም።
.
ይቀጥላል...........

ይቀላቀሉን ይቀላቀሉን

@eslamik_tube