Get Mystery Box with random crypto!

°• ማኅቶት ፕሮሞሽን°• 'እግዚአብሔር የፈጠራቸው ፍጥረታት በሙሉ ለሰው ውስጣዊና ውጫዊ ተፈጥ | አፄ እስያኤል

°• ማኅቶት ፕሮሞሽን°•



"እግዚአብሔር የፈጠራቸው ፍጥረታት በሙሉ ለሰው ውስጣዊና ውጫዊ ተፈጥሮ እንዲስማሙ ተደርገው የተፈጠሩ ናቸው። ለምሳሌ ውሃ የተፈጠረው አስቀድሞ በሰው ውስጥ የመጠ'ማት ስሜት ስለሚገኝ ነው። ውሃ ትርጉም የኖረው የሚጠጣ አካል በመኖሩ ሲሆን፤ እህልም ትርጉም ያገኘው የሚመገብ ሠው በመፈጠሩ ነው። ምግብ ከውጭ ሲፈጠር ከሠው ውስጥ ደግሞ የመራብ ስሜት ተፈጥሯል። የሚሰ'ማ ድምፅ ሲፈጠር በሠው ውስጥ ደግሞ መስማት አለ። ድምፅ ትርጉም ያገኘው የሚሰማ ጆሮ በመፈጠሩ ሲሆን አየር (ኦክስጅን) ደግሞ ትርጉም ያገኘው የሚተነፍስ ሳንባ ስለተፈጠረ ነው።
.
ሊቃውንት "ፍጥረታት በጠቅላላ በመጠን፣ በመጠን ተቆንጥረው በሠው ውስጥ አሉ" ይላሉ። አስራው (አራቱ) ፍጥረታት የሚባሉት እሳት፣ ውሃ፣ ነፋስ፣ መሬት በሠው ውስጥ አሉ። ዕፅዋትና እንስሳት ሠውም ከእነዚህ ተገኝተዋል። ከእነዚህ ከአራቱ ያልተገኘ ፍጥረት የለም። በዚህ ስሌት መሠረት ሁሉም ፍጥረታት በሠው ውስጥ አሉ። ስለዚህ የአጠቃላይ ፍጥረታት መፈጠርን ትርጉም እንዲኖረው ያደረገው የሠው መፈጠር ሲሆን፤ ሠውም በውጫዊውም ሆነ በውስጣዊው ፍላጎቱ ከሌሎች ፍጥረታት ጋር ግንኙነት እንዲኖረው ተደርጎ ተፈጥሯል።"
--------------
|| ☞ 'ርጢን' ገጽ 26 - 2



╚» open open«╝ - ╚» open open «╝
➶➶➶➶➶ open open open open ➷➷➷➷➷
ıllıllı open open open open ıllıllı
|I{•------» open open «------•}I|

ከስር ያሉትን ቻናሎች እንዲከተሉልን በእግዚአብሔር ዘንድ እንጠይቃለን