Get Mystery Box with random crypto!

በቆቦ ከተማ በሲቪል ሰዎች ላይ ያነጣጠረው ጥቃት አሳሳቢ መሆኑ ተገለፀ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብ | Esat News

በቆቦ ከተማ በሲቪል ሰዎች ላይ ያነጣጠረው ጥቃት አሳሳቢ መሆኑ ተገለፀ

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን (ኢሰማኮ) በቆቦ ከተማና በዙሪያው ካሉ የገጠር ከተሞች የሚደርሱትና በህወሓት ሃይሎች እንደተፈፀመ የሚነገር በሲቪል ሰዎች ላይ ያነጣጠረ ጥቃት በእጅጉ የሚያሳስብ መሆኑን ገልጿል።

የሲቪል ሰዎች መኖሪያ አካባቢዎችን ፣ የቤት ለቤት አሰሳና ግድያ ፣ ዝርፊያና የመሰረተ ልማቶች ጥቃት ጭምር መፈፀሙን ለሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ሪፖርት መድረሱን ብስራት ራዲዮ ሰምቷል።

ኮሚሽኑ የሚያደርገውን ምርመራ እንደሚቀጥልና በግጭቱ ሁሉም ወገኖች በማናቸውም ወቅት ሲቪል ሰዎችን የመጠበቅ ፣ ያለባቸው ግዴታ እንዲያከብሩ በጥብቅ አሳስቧል።

@Esat_tv1
@Esat_tv1