Get Mystery Box with random crypto!

በክተት ዐዋጅ ስሟን የጠሯት አፍጣኒተ ረድኤት የኾነችው የእመቤታችንን ታቦትና የፍጡነ ረድኤት የቅዱ | ኤጲፋንዮስ🌹

በክተት ዐዋጅ ስሟን የጠሯት አፍጣኒተ ረድኤት የኾነችው የእመቤታችንን ታቦትና የፍጡነ ረድኤት የቅዱስ ጊዮርጊስን ታቦት አስይዘው በመኼድ የካቲት 23 በ1888 ዓ.ም. የጣሊያንን ጦር በመደምሰስ እጅግ አስደናቂ ድልን በአህጉሪቱ በአፍሪካ በማስመዝገብ ለመላው የአፍሪካ ሕዝቦች የነጻነት ጮራ ዋና ወጊ በመኾን፤ መላው አፍሪካ የተጫነበትን የቅኝ ግዛት ቀንበርንና የነጮችን የበላይነት ሰባብሮ እንዲጥል መርህ ኾነውታል፤ በእውነት ስሟን የጠሯት ወላዲተ አምላክ አላሳፈረቻቸውም፤ ይኽ ፍቅራቸው በልጃቸው በንግሥተ ንግሥታት ዘውዲቱ ዐልፎ በአታ ለማርያምንና ሌሎች የእመቤታችንን መቅደስ አሠርተው፤ በሚያልፍ ዘመን የማያልፍ ሥራ ሠርተው ወደ ልዑል እግዚአብሔር ተጠርተው ኼደዋል፨

[በመጨረሻም ጽሑፌን ዐጼ ምኒልክን በቃል ኪዳኗ የተራዳችውን እመቤታችንን፤ በፈጣን ተራዳኢነቱ ያልተለያቸው ሊቀ ሰማዕታት ቅዱስ ጊዮርጊስን አስቀድሞ በ530 ዓ.ም. ባመሰገነው በቅዱስ ያሬድ ቃል አበቃለሁ፦
"ስብሐት ለእግዚአብሔር በሰማያት ወላዕሌነ ይኩን ምሕረት በጸሎተ ጊዮርጊስ ዐቢይ ሰማዕት ወማርያም ወላዲተ አምላክ" [በሰማያት ለአምላካችን ለእግዚአብሔር ምስጋና ይኹን በታላቁ ሰማዕት በጊዮርጊስና አምላክን በወለደች በእመቤታችን ጸሎት የእግዚአብሔር ምሕረት በእኛ ላይ ይኹን] [ቅዱስ ያሬድ]
ከሌሊቱ 6 ሰዓት የካቲት 23 በሞባይሌ ላይ ለበረከት ያኽል በጥቂቱ ጻፍኩት [መጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ] [በድጋሚ ፓስት አረኩት]