Get Mystery Box with random crypto!

ጎዶሎ አዳም አለ ። (ካሊድ አቅሉ) አሲድ ተደፋባት፣ መልኳ ተበላሸ እጇ አልቀረ ጡትዋ፤ በመኝታ | የግጥም ጣዕም ✍

ጎዶሎ አዳም አለ ።
(ካሊድ አቅሉ)

አሲድ ተደፋባት፣ መልኳ ተበላሸ
እጇ አልቀረ ጡትዋ፤
በመኝታ ብዛት ቦታ ስትዋል ባትዋ፤
ልጇ አለየቻትም! እናትና አባትዋ ሰርክ
ያነባሉ
ጎረቤት ሲመጣ ከንፈር በመምጠጡ
ይጨናነቃሉ
ባልየዋ ታስርዋል እድሜ ልክ መሰለኝ
ይሄ ሁሉ ሲሆን ግን እኔን የጨነቀኝ
እንዲህ የራሩላት ዘመድ ከጎረቤት
መርዙ ከላይዋ ላይ ስለሆነ ነው ከፊት ።

ስንት ሴቶች አሉ ልቤን የሚበሉኝ
ባየዋቸው ቁጥር የሚያንገበግቡኝ
ገፃቸው ያማረ አፈጣጠራቸው ብዙ
የተወደደ
ከሙሉዎች መሀል ጎዶሎ አዳም አለ፤
መልካቸውን ትቶ ልባቸው ላይ ክህደት
አርከፍክፎ የሄደ !

(የሳቁ ሁሉ ደስተኞች አይደሉም )
@kalidakelu