Get Mystery Box with random crypto!

የአራት ሰው ሠራዊት ነበዩ ኤልሳዕ በነበረበት ዘመን ከተፈጸሙ በርካታ ተአምራት መካከል በመጽሀፈ | ፍኖተ-ወራዙት ዘኦርቶዶክስ ⛪

የአራት ሰው ሠራዊት

ነበዩ ኤልሳዕ በነበረበት ዘመን ከተፈጸሙ በርካታ ተአምራት መካከል በመጽሀፈ ነገሥት ካልዕ ምእራፍ 7 ላይ ያለው ታሪክ ይገኛል። በዚህ የመፅሀፍ ክፍል ላይ እንደምናገኘው ሶርያውያን ሰማርያን ከበው እጅግ ታላቅ ረሃብ ተነሳ። ጽኑዕ ረሃብም ህዝቡን ፈተነ፡፡ የእግዚአብሔርን ቃል የሚሰማ ጻድቅ በእነርሱ ዘንድ ነበርና ለረሃቡ ዘመን ማብቂያ የሚሆን ብስራት በቅዱሱ ኤልሳዕ ከተነገረ በኋላ በንጉሡ ደጃፍ የነበረው አለቃ በእግዚአብሔር መልካምነት ላይ የማይገባውን ተናገረ። በቸርነቱም ላይ ዘበተ። ቅዱሱም የእግዚአብሔር ሰው ኤልሳዕ ባለስልጣኑን ' ታየዋለህ እንጂ አትበላውም!' አለው። ብዙ ሰዎች የእግዚአብሔርን ቸርነት የምንመዝነው በእኛ የንፉግነት ሚዛን ፍቅሩንም በክፋታችን መለኪያ ልክ ነውና በዚህም ፈጽመን እንስታለን ለጥፋትም እንደርሳለን፡፡

የእግዚአብሔር ቃል መፈጸሙ አይቀርም። ረሃብ ያስጨነቃቸው ቁጭ ብለው መሞትን ለመጠበቅ እምቢ ያሉ አራት ለምጻም ሰዎች ጨለማውን ተገን አድርገው ሞትን ደፍረው ወደ ሶርያውን ሰፈር ተጠጉ። ወደ ዳርቻው በተጠጉ ጊዜሜ እግዚአብሔር የእነዚህን ሰዎች የኮቴ ድምጽ በሶርያውያን ጆሮ የፈረስ እና የሠራዊት ድምጽ አድርጎ አሰማቸው። እነርሱም 'እነሆ የእስራኤሉ ንጉሥ ግብጻውያንን እና ኬጢያውያንን አሰልፎ መጥቶብናል' ብለው ምግባቸውን ጥለው ሸሹ። እስራኤልም ከምግቡ ጠገቡ ÷ የበረከቱን ስራ የናቀውም ባለስልጣን ተረግጦ በረከቱን ተመለከተ እንጂ ሳይበላው ሞተ ፡፡ የእነዚህ የአራቱን ሰዎች ሠራዊት ነገር እንዴት ይደንቅ?! ዘመኑ በልጅ እንኳ አስጨክኖ ልጅን ያስበላ ረሃብ ይባስ ብሎ እነርሱ ከህዝብ ጋር መቀላቀል የማይችሉ : በህመማቸው ምክንያት ከህዝቡ ተለይተው ለመኖር የተፈረደባቸው ድውያን! እግዚአብሔር ግን ለህዝቡ ያለውን ምህረት በእነርሱ በኩል ገለጸ። እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ካለ ማንስ ሊቃወመን ይችላል?! እርሱ ያበረታውን ክንዳችንን ማን ሊያጥፈው ÷ ያሠመረውን መንገዳችንን ማን ሊዘጋ ይቻለዋል?! ይህ የአራት ሰው ሰራዊት በማሸበሩ የታወቀውን የወልደአዴርን ጦር በቀን ሳይሆን በምሽት ንብረቱን ጥሎ አሳደደው ÷ በረከቱም ለህዝቡ ሆነ ። እኛም እንዲህ እንላለን፡

'ጌታ ሆይ! የነፍሳችን ረሃብ አስጨንቆናል። ጠላታችን ዙሪያችንን ከቦ ያስጨንቀናል የፈረሶቹ እና የሰረገሎቹ ድምጽ ይሰማናልና እባክህን በኃጥያት ለምጽ ወደ ነደደው ማንነታችን ቅረብ ÷ አንተ ካለህ በትንሹ ነገር እንበረታለንና!'

ወነአምን በአሐቲ ቅድስት ቤተክርስቲያን

https://t.me/negerlikawunt