Get Mystery Box with random crypto!

ቃሉን እንማር

የቴሌግራም ቻናል አርማ endashaw_negash — ቃሉን እንማር
የቴሌግራም ቻናል አርማ endashaw_negash — ቃሉን እንማር
የሰርጥ አድራሻ: @endashaw_negash
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 5.28K
የሰርጥ መግለጫ

ይህ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርት እና ስብከት የሚቀርብበት ቻናል ነው። ቃሉን በመፈለግ በመኖር እና በማስተማር እንትጋ!
Find me on my YouTube Channel:
https://www.youtube.com/channel/UCNz7MqCOz-nl0B5SITmKMHQ/featured

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-09-01 06:20:18 ነሐሴ 26 ቀን፣ 2014
የንባብ ክፍል፡- ሚክያስ 1፣ 2 እና 3

ሚክያስ 1፤ በይሁዳ ነገሥታት በኢዮአታም፣ በአካዝና በሕዝቅያስ ዘመን ወደ ሚክያስ የመጣው የእግዚአብሔ ቃል፤ በሰማርያ እና በኢየሩሳሌም ላይ የእግዚአብሔር ፍርድ ይገለጣል፤ ሰማርያ የፍርስራሽ ክምር ትሆናለች፤ በዚህ ምክንያት አለቅሳለሁ፤ ዋይ ወይም እላለሁ፤ እስከ ኢየሩሳሌም በር ሳይቀር ክፉ ነገር ከእግዚአብሔር ዘንድ መጥቷል።

ሚክያስ 2፤ ክፉ ለመሥራት ለሚያቅዱ፣ በመኝታቸው ሳሉ ተንኮል ለሚያውጠነጥኑ ወዮላቸው፤ ሲነጋ ይፈጽሙታል፤ ጥፋት ላመጣ ዐቅጃለሁ፤ ሐሰተኛ ነቢያትን ተቀበላችሁ፤ ያዕቆብን እሰበስባለሁ፤ የእስራኤልንም ትሩፍ በአንድነት አመጣለሁ፤ ሰባሪው በፊታቸው ይሄዳል፤ ሰብረው ወጥተው ይሄዳሉ፤ እግዚአብሔር ይመራቸዋል።

ሚክያስ 3፤ መሪዎች፣ ገዦች ስሙ፤ መልካሙን ጠላችሁ ክፉውንም ወደዳችሁ፤ የሕዝቤን ሥጋ በላችሁ፤ ቆዳቸውን ገፈፋችሁ፤ ሕዝቤን የሚያስቱ ነቢያት ሰው ሲያበላቸው ሰላም አለ ይላሉ፤ ሳያበላቸው ሲቀር ጦርነት ያውጁበታል፤ ለያዕቆብ በደሉን፣ ለእስራኤልም ኀጢአቱን እነግር ዘንድ በእግዚአብሔር መንፈስ ፍትሕና ብርታት ተሞልቻለሁ፤ መሪዎች በጉቦ ይፈርዳሉ፣ ካህናት ለዋጋ ያስተምራሉ፣ ነቢያት ለገንዘብ ይናገራሉ፤ ፅዮን ትታረሣለች።

ከተማርኩት፡-
 የእግዚአብሔር ፍርድ እንደሚገለጥ ሲናገር፣ “ይህ ሁሉ የሚሆነው ስለ ያዕቆብ በደል፣ ስለ እስራኤልም ቤት ኀጢአት ነው” ይላል።
 “ክፉ ለመሥራት ለሚያቅዱ፣ በመኝታቸው ሳሉ ተንኮል ለሚያውጠነጥኑ ወዮላቸው! ሲነጋ በማለዳ ይፈጽሙታል፤ የሚያደርጉበት ኀይል በእጃቸው ነውና።”
 “የያዕቆብ ቤት ሆይ፤ እንዲህ ሊባል ይገባልን? “የእግዚአብሔር መንፈስ የማይታገሥ ነውን? እንዲህ ያሉት ነገሮችስ ያደርጋልን? መንገዱ ቀና ለሆነ ቃሌ መልካም አያደርግምን?”
 በእርግጥ ሁላችሁንም እሰበስባለሁ! “የሚሰብረው ወጥቶ በፊታቸው ይሄዳል፤ እነርሱም በሩን በመስበር ወጥተው ይሄዳሉ፤ እግዚአብሔር እየመራቸው ንጉሣቸው ቀድሞአቸው ይሄዳል።”
 መሪዎችን ሲገሥጽ “መልካሙን ጠላችሁ ክፉውንም ወደዳችሁ፤ የሕዝቤን ቆዳ ገፈፋችሁ፤ ሥጋቸውንም ከዐጥንቶቻቸው ለያችሁ፤ …“ ስለ ነቢያት ሲናገር፣ ሰው ሲያበላቸው ሰላም አለ ይላሉ፤ ሳያበላቸው ሲቀር ግን ጦርነት ሊያውጁበት ይነሣሉ” ይላል።
 “እኔ ግን ለያዕቆብ በደሉን፣ ለእስራኤልም ኀጢቱን እነግር ዘንድ ኀይልን፣ በእግዚአብሔር መንፈስ ፍትሕና ብርታት ተሞልቻለሁ።”
 “መሪዎች በጉቦ ይፈርዳሉ፤ ካህናት ለዋጋ ሲሉ ያስተምራሉ፤ ነቢያቷም ለገንዘብ ሲሉ ይናገራሉ። … ስለዚህ በእናንተ ምክንያት ጽን እንደ እርሻ ትታረሳለች፣ ኢየሩሳሌም የፍርስራሽ ክምር ትሆናለች፤ …”

ቃሉን እንጸልይ፡-

እግዚአብሔር መልካም መልካሙን ብቻ ሳይሆን ችግሮቻችንን በግልጽ በሚነግሩን አገልጋዮች ይባርከን! ጸጋ ይብዛልን!
439 views03:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 21:05:58
Miss it Not!
622 views18:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 06:26:37
ነሐሴ 25
645 views03:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 07:03:25
ነሐሴ 24
ሙሉውን መጽሐፍ ቅዱስ በአንድ ዓመት አንብበን ለመጨረስ የቀረን ቀን የቀረን የ11 ቀን ንባብ ብቻ ነው! Praise be to the Lord!
587 views04:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 16:24:30 የኅትመት ዋጋ ጣሪያ ነክቷል! The cost of the printing has skyrocketed!ለአንድ ሺህ ቅጂዎች 333,000 ብር ሊከፈል መሆኑን ማን ያምናል? ባይታተምስ ብያስብልም ዓመቱን በሙሉ የተለፋበት ነውና ሊወለድ ግድ ይላል!

ልንረከበው አራት ቀን፣ መርቀን በይፋ ለንባብ ልናቀርበው ስድስት ቀን ቀርቷልና ርብርብ ይፈልጋል። በማይጠበቁ ሰዎች ሥራውን የጀመረው እግዚአብሔር እንደሚጨርሰው አምናለሁ።

Back to the Word! በ2015 ዓ.ም እንዲቀጣጠል እና በአብያተ ክርስቲያናት ሁሉ እንዲሠራጭ እንጸልይ!
ለአዲስ ዓመት ይህን መጽሐፍ ሥጦታ መስጠት ማለት ወዳጃችሁ ዓመቱን በሙሉ መጽሐፍ ቅዱስ እንዲያነብ መርዳት ነው።

የሥራው ባለቤት የሆነው እርሱ እንደ ባለጠግነቱ መጠን ይባርካችሁም!
626 views13:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 06:15:31 ነሐሴ 23 ቀን፣ 2014
የንባብ ክፍል፡- አሞጽ 4. 5 እና 6

አሞጽ 4፤ ድኾችን የምትጨቁኑና ችግረኞችን የምታስጨንቁ እግዚአብሔር ይቀጣችኋል፤ ሆዳችሁን ቦዳ አደረግሁት፤ የምትበሉትን አሳጣኋችሁ፤ መቅሠፍት ላክሁባችሁ፣ ወዘተ. እናንተ ግን ወደ እኔ አልተመለሳችሁም፤ እንደዚህ ስለማደርግብህ አምላክህን ለመገናኘት ተዘጋጅ።

አሞጽ 5፤ እኔን ፈልጉ በሕይወት ትኖራላችሁ፤ ፍትሕን ወደ መራርነት የምትለውጡ፣ ጽድቅን ወደ ምድር የምትጥሉ ወዮላችሁ! እግዚአብሔር በብርቱው ላይ ድንገተኛ ጥፋት ያመጣል፤ የሚገሥጻችሁን ትጠላላችሁ፤ ጻድቁን ትጨቁናላችሁ፤ ጉቦ ትቀበላላችሁ፤ ክፉውን ጥሉ፤ መልካሙን ውደዱ፤ ፍትሕን አታጉድሉ፤ የእግዚአብሔርን ቀን ለምትሹ ወዮላችሁ፤ ዓመት በዓላችሁን ተጸይፌያለሁ፤ እንድትሰደዱ አደርጋለሁ።

አሞጽ 6፤ በጽዮን ተዘልላችሁ የምትቀመጡ እናንተ የአሕዛብ አለቆች ወዮላችሁ፤ በመጀመሪያ በምርኮ ከሚወሰዱ መካከል ናችሁ፤ የያዕቆብን ትዕቢት ተጸይፌያለሁ፤ ፍትሕን ወደ መርዝነት፣ የጽድቅንም ፍሬ ወደ መራርነት ለወጣችሁ፤ የሚያስጨንቃችሁን ሕዝብ በእናንተ ላይ አስነሣለሁ።

ከተማርኩት፡-
 እግዚአብሔር ድኾችን የሚጨቁኑትንና ችግረኞችን የሚያስጨንቁትን ይመለከታል፤ ደግሞም ይቀጣል!
 “… እናንተ ግን ወደ እኔ አልተመለሳችሁም … አምላክህን ለመገናኘት ተዘጋጅ!”
 “እኔን ፈልጉ በሕይወት ትኖራላችሁ። … እግዚአብሔርን ፈልጉ በሕይወት ትኖራላችሁ፤ …”
 “እናንተ ፍትሕን ወደ መራርነት የምትለውጡ፣ ጽድቅንም ወደ ምድር የምትጥሉ ወዮላችሁ!”
 “… ጻድቁን ትጨቁናላችሁ፤ ጉቦም ትቀበላላችሁ፤ በፍርድ አደባባይም ከድኻው ፍትሕ ትነጥቃላችሁ።”
 “ስለዚህ አስተዋይ ሰው በእንዲህ ያለ ጊዜ ዝም ይላል፤ ቀኖቹ ክፉዎች ናቸውና።”
 “በሕይወት ትኖሩ ዘንድ መልካሙን እንጂ ክፉውን አትፈልጉ፤ ከዚያ በኋላ እንደ ተናገራቸሁት የሰራዊት አምላክ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ይሆናል።”
 “ክፉውን ጥሉ፤ መልካሙንም ውደዱ፤ በፍርድ አደባባይ ፍትሕን አታጓድሉ፤ …”
 እግዚአብሔር በዓላቸውን እንደ ተጸየፈ፣ መሰብሰባቸው ደስ እንደማያሰኘው፣ መሥዋዕታቸውን እንደማይቀበል፣ ዝማሬያቸውን እንዲያርቁለት ከተናገረ በኋላ፤ “ነገር ግን ፍትሕ እንደ ወንዝ፣ ጽድቅም እንደማይደርቅ ምንጭ ይፍሰስ” ይላቸዋል። እርሱ ግብዝነት በሞላበት ሃይማኖታው ሥርዐት አይታለልም!
 እግዚአብሔር “የያዕቆብን ትዕቢት ተጸይፌአለሁ” ይላል።

ቃሉን እንጸልይ፡-

እግዚአብሔር በማኅበረ ሰቡ ላይ ምንም ተጽእኖ የሌለው እና በግብዝነት የተሞላ ሃይማኖታዊ ሥርዐት ከመፈጸም ይጠብቀን! ጸጋ ይብዛልን!
631 views03:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 06:49:07
ነሐሴ 22 ደርሰናል! ጸጋ ይብዛልን!
622 views03:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 06:11:26
የዛሬው የጥሞና ክፍል ከመጽሐፉ (በከፊል) የተወሰደ ነው። ጸጋ ይብዛላችሁ!
701 views03:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 06:42:31 ነሐሴ 20 ቀን፣ 2014
የንባብ ክፍል፡- ሆሴዕ 11፣ 12፣ 13 እና 14

ሆሴዕ 11፤ እስራኤል ግን አብዝቼ በጠራኋቸው ቁጥር አብዝተው ከእኔ ራቁ፤ አስተማራቸው፣ ፈወሳቸው፣ በፍቅር ሰንሰለት ሳባቸው፣ እነርሱ ግን ንስሓ መግባትን እምቢ አሉ፤ ዘወር ማለትን መረጡ፤ ኤፍሬም ሆይ፤ እንዴት እጥልሃለሁ? እስራኤል ሆይ፤ እንዴት አሳልፌ እሰጥሃለሁ? እግዚአብሔር ለእስራኤል ያለው ፍቅር! 

ሆሴዕ 12፤  ኤፍሬም ሐሰትንና ዐመፅን ያበዛል፤ ተመለስ፤ ፍቅርንና ፍትሕን ጠብቅ፤ ዘወትር በአምላክህ ታመን፤ ነጋዴው ያጭበረብራል፤ መታበይ አለ፤ እግዚአብሔር ስለ ንቀቱ የሚገባውን ይከፍለዋል።

ሆሴዕ 13፤ ኀጢአት መሥራት አበዙ፤ ብራቸውን አቅልጠው ለራሳቸው ጣዖት ሠሩ፤ ከእኔ በቀር ሌላ አዳኝ የለም፤ ጠገቡ፤ ታበዩ፤ እግዚአብሔርን ረሱ፤ የእግዚአብሔር ቁጣ በእስራኤል ላይ ይገለጣል። 

ሆሴዕ 14፤ እስራኤል ሆይ፤ በኀጢአትህ ምክንያት ስለ ወደቅህ ወደ አምላክህ ወደ እግዚአብሔር ተመለስ፤ ይቅር በለን፤ በምሕረትህ ተቀበለን በሉት፤ እግዚአብሔር እንደሚወዳቸውና ተሐድሶን እንደሚያደርግ ተናገረ፤ የምሰማህና የምጠነቀቅልህ እኔ ነኝ፤ የእግዚአብሔር መንገድ ቅን ነው፤ ጻድቃን ይሄዱበታል፤ ዐመፀኞች ግን ይሰናከሉበታል።  

ከተማርኩት፡- 
“እስራኤል ገና ሕፃን ሳለ ወደድሁት፤ ልጄንም ከግብፅ ጠራሁት። እስራኤል ግን አብዝቼ በጠራኋቸው ቁጥር አብዝተው ከእኔ ራቁ፤ … ኤፍሬምን እጁን ይዤ እንዲራመድ ያስተማርሁት እኔ ነበርሁ … በፍቅር ሰንሰለት ሳብኋቸው፤ … ዝቅ ብዬ መገብኋቸው።” እግዚአብሔር ለሕዝቡ ያሳየው ፍቅር አስደናቂ ነው።
የሕዝቡ በደል፣ ዐመፅ በዝርዝር የቀረበበት መንገድ የሚገርም ነው። የሕዝቡ ዐመፅ እና የእግዚአብሔር ትዕግሥት፣ ፍቅር በንጽጽር ይታያል!
“ኤፍሬም ሆይ፤ እንዴት እጥልሃለሁ? እስራኤል ሆይ፤ እንዴትስ አሳልፌ እሰጥሃለሁ? … ልቤ በውስጤ ተናወጠ፤ ምሕረቴም ሁሉ ተነሣሥቶአል።”
“ስለዚህ ወደ አምላክህ ተመለስ፤ ፍቅርንና ፍትሕን ጠብቅ፤ ዘወትርም በአምላክህ ታመን።”
“እኔ ግን ከግብፅ ምድር ያወጣሁህ አምላክህ እግዚአብሔር ነኝ፤ ከእኔ በቀር ሌላ አምላክ አታውቅም፤ ከእኔም በቀር ሌላ አዳኝ የለም። በምድረ በዳ በሐሩር ምድርም ተንከባከብሁህ። ካበላኋቸው በኋላ ጠገቡ፤ በጠገቡ ጊዜ ታበዩ፤ ከዚያም ረሱኝ።” 
“ከመቃብር ኀይል እታደጋቸዋለሁ፤ ከሞትም እቤዣቸዋለሁ፤ ሞት ሆይ፤ መቅሠፍትህ የት አለ? መቃብር ሆይ፤ ማጥፋትህ የት አለ? …”
ኀጢአታችንን ይቅር በለን፤ በምሕረትህ ተቀበለን ብላችሁ ወደ እግዚአብሔር ተመለሱ የሚለው ጥሪ አስተማሪ ነው። 
“… የምሰማህና የምጠነቀቅልህ እኔ ነኝ፤ … ፍሬያማነትህም ከእኔ የተነሣ ነው። ጥበበኛ የሆነ እነዚህን ነገሮች ያስተውላል፤ አስተዋይም እነዚህን ነገሮች ይረዳል።”
“የእግዚአብሔር መንገድ ቅን ነውና፤ ጻድቃን ይሄዱበታል፤ ዐመፀኖች ግን ይሰናከሉበታል።” 

ቃሉን እንጸልይ፡- 

ፍሬያማ የሚያደርገን እና የሚጠነቀቅልን የፍቅር አምላክ እግዚአብሔር ስሙ ይባረክ! ጸጋ ይብዛልን! 
734 views03:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-25 06:55:04 ነሐሴ 19 ቀን፣ 2014
የንባብ ክፍል፡- ሆሴዕ 7፣ 8፣ 9 እና 10

ሆሴዕ 7፤ ሁሉም አመንዝራ ናቸው፤ ከእነርሱም ወደ እኔ የቀረበ ማንም የለም፤ ኤፍሬም ከአሕዛብ ጋር ተደባለቀ፤ ኤፍሬም ያልተገላበጠ ቂጣ ነው፤ ወደ አምላኩ አልተመለሰም፤ በቀላሉ እንደሚታለል ርግብ ነው፤ ከእኔር ርቀው ሄደዋልና ጥፋት ይመጣባቸዋል፤ እኔ አሠለጠንኋቸው እነርሱ ግን አደሙብኝ፤ መሪዎቻቸው በሰይፍ ይወድቃሉ። 

ሆሴዕ 8፤ እስራኤል በጎ የሆነውን ነገር ናቁ፤ ጣዖታትን ለራሳቸው ሠሩ፤ ነፋስን ይዘራሉ፤ ዐውሎ ነፋስንም ያጭዳሉ፤ በአሕዛብ መካከል ዋጋ እንደ ሌለው ዕቃ ሆነዋል፤ እግዚአብሔር ይቀጣቸዋል።   

ሆሴዕ 9፤ በእስራኤል ላይ የቅጣት ቀን መጥቶአል፤ የፍርድም ቀን ቀርቦአል፤ ነቢዩ እንደ ሞኝ፣ መንፈሳዊውም ሰው እንደ እብድ ተቆጥሮአል፤ ለነፍሰ ገዳዮች አሳልፎ ይሰጣቸዋል፤ ባለመታዘዛቸው አምላኬ ይጥላቸዋል።

ሆሴዕ 10፤ ኤፍሬም ይዋረዳል፤ እስራኤልም ስለ ጣዖቱ ያፍራል፤ ክፋትን ዘራችሁ፤ ኀጢአትንም ዐጨዳችሁ፤ የሐሰትንም ፍሬ በላችሁ፤ ምሽጎችህም ሁሉ ይፈራርሳሉ፤ የእስራኤል ንጉሥ ፈጽሞ ይጠፋል። 

ከተማርኩት፡- 
“ንጉሥን በክፋታቸው፣ አለቆችንም በሐሰታቸው ያስደስታሉ።”
“ኤፍሬም በቀላሉ እንደምትታለል አእምሮም እንደሌላት ርግብ ነው፤ አንድ ግዜ ወደ ግብፅ ይጣራል፤ ሌላ ጊዜ ደግሞ ወደ አሦር ይዞራል።”
“ነገር ግን እስራኤል በጎ የሆነውን ነገር ናቁ፤ ጠላትም ያሳድዳቸዋል።” ያለ እግዚአብሔር ፈቃድ ንጉሥ በማንገሥ፣ ጣዖታትን ለራሳቸው ሠርተው በማምለክ፣ በሌሎች በመታመን፣ ወዘተ. በድለዋል።
“እስራኤል ፈጣሪውን ረሳ፤ …” ስለ ሠሩት ኀጢአት እግዚአብሔር አሳልፎ ሰጣቸው!  
“ለራሳችሁ ጽድቅን ዝሩ፤ የጽኑ ፍቅርን ፍሬ ዕጨዱ፤ … ጽድቅን በላያችሁ እስኪያዘንብ ድረስ እግዚአብሔርን የምትፈልጉበት ጊዜ ነውና።”
እግዚአብሔርን አለመስማት ውጤቱ አደገኛ ነው፤ የእግዚአብሔር ቅጣት/ፍርድ ሲገለጥ በፊቱ ሊቆም የሚችል የለም!

ቃሉን እንጸልይ፡- 

እግዚአብሔር ሲናገር ያልሰማ ፍርዱ ሲገለጥ ማምለጫ የለውም! ጸጋ ይብዛልን! 
692 views03:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ