Get Mystery Box with random crypto!

ልጁን መምሰል በዚህ በወደቀ ዓለም ውስጥ አሁን አሁን ሚሰሙ ይሄማ እብደት ነው የሚያስብሉ ነገሮች | El OlaM ▣

ልጁን መምሰል

በዚህ በወደቀ ዓለም ውስጥ አሁን አሁን ሚሰሙ ይሄማ እብደት ነው የሚያስብሉ ነገሮች እጅጉን ጨምረዋል የሚወዱትን Celebrity ለመምሰል መላ ፊታቸውን የሚያስቀይሩ ምስኪን አይሉአቸው ሞኝ ሰዎች ጥቂት አይደሉም በጣም በእነሱ ፍቅር ከመጠናወታቸው የተነሳ የነሱ የልጅነት መልክ አያሳስባቸውም

በራሳቸው ገንዘብ የራሳቸውን መልክ ያጠፉታል ያውም ለማያቃቸው መፈጠራቸውን እንኳ ለማያቅ ተራ ሰው አንድ ሰውን ለመምሰል እኮ ግዴታ ፊትህን ማስቀየር ድረስ መሄድ አያስፈልግም የልብስ ፋሽን እና ባህሪ መውሰድ በቂ ነው ለእነዚህ አይነት ሰዎች ግን የፍቅራቸው ጥግ መልክን እስከመተው ነው

and That made me think we Christians ለካ በደምብ ክርስቶስን መምሰል አልገባንም ለካ እሱን መምሰል ማለት የራስን መልክን ማጥፋት ነው ባለን አቅም ሙጭጭ አድርገን እሱን ፊታችን ላይ ለመሳል መጣጣር ነው ፍጥረታዊ ሰው እንኳ ለማያውቀው አንድ ተራ ሰው እንዲህ ከሆነ እኛማ አብዝቶ ለሚያቀን ደግሞ ለሚወደን እንዲህ አለመሆናችን ያሳዝናል

Like Augustine said " Christian is a mind through which Christ thinks,a heart through which christ loves,a voice through which christ speaks,a hand through which christ helps."

እግዚአብሔር ልጁን እንድንመስል ይርዳን!